ምሳሌ 6:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታዲያ፥ አንተ ሰነፍ! የምትተኛው እስከ መቼ ነው? ከእንቅልፍህስ የምትነቃው መቼ ነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተ ሰነፍ፤ እስከ መቼ ትተኛለህ? ከእንቅልፍህስ መቼ ትነሣለህ? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተ ሰነፍ፥ እስከ መቼ ትተኛለህ? ከእንቅልፍህስ መቼ ትነሣለህ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንተ ታካች እስከ መቼ ትተኛለህ? ከእንቅልፍህስ መቼ ትነሣለህ? |
“እናንተ ዕውቀት የጐደላችሁ! እስከ መቼ ድረስ የሞኝነትን መንገድ ትከተላላችሁ! እናንተስ ፌዘኞች! እስከ መቼ ድረስ በማፌዝ ትደሰታላችሁ! ሞኞችስ እስከ መቼ ድረስ ዕውቀትን ትጠላላችሁ!
እንግዲህ ከእንቅልፍ የምትነቁበት ሰዓት አሁን መድረሱን ዕወቁ፤ በፊት ካመንበት ጊዜ ይልቅ አሁን የምንድንበት ቀን ይበልጥ ወደ እኛ ቀርቦአል።