ከመጠን በላይ በሆነው ሞኝነቱ መንገዱን ይስታል፤ ራሱን መቈጣጠር ካለመቻሉ የተነሣ ይሞታል።
ከተግሣጽ ጕድለት የተነሣ ይሞታል፤ ከቂልነቱ ብዛት መንገድ ይስታል።
አልተቀጣምና እርሱ ይሞታል፥ በአላዊቅነትም ብዛት ይስታል።
እርሱ ከሰነፎች ጋር ይሞታል፤ ከስንፍናውም ብዛት የተነሣ ሕይወቱ ይጣላል፤ ስለ ስንፍናውም ይጠፋል።
እርሱን ካልሰሙት በሰይፍ ይጠፋሉ፤ በድንቊርና እንዳሉም ይሞታሉ።
ካስማው እንደ ተነቀለ ድንኳን ያለ ጥበብ ይሞታሉ።’ ”
ስለዚህ በልበ ደንዳናነታቸው አካሄድ እንዲሄዱ፥ የፈለጉትንም ነገር እንዲያደርጉ ተውኳቸው።
እርሱ ስለ ክፋታቸው ይቀጣቸዋል፤ ስለ ኃጢአታቸውም ይደመስሳቸዋል፤ እግዚአብሔር አምላካችን ያጠፋቸዋል።
ስለዚህ የሚገባችሁን ቅጣት ትቀበላላችሁ፤ የተንኰላችሁንም ውጤት ታገኛላችሁ።
የደግ ሰው ንግግር ብዙ ሰዎችን ይጠቅማል፤ ሞኞች ግን ከማስተዋል ጒድለት የተነሣ ይሞታሉ።
ሰው በጥበቡ ይመሰገናል፤ አስተሳሰቡ ጠማማ የሆነ ሰው ግን ይናቃል።
ከሐዲዎች ሰዎች የክፉ ሥራቸውን ዋጋ ይቀበላሉ፤ ደጋግ ሰዎች ግን የመልካም ሥራቸውን ዋጋ ያገኛሉ።
ችግር ሲመጣ ክፉዎች ይወድቃሉ፤ ጻድቃን ግን በታማኝነታቸው ይጠበቃሉ።
ከማስተዋል መንገድ የሚርቀውን ሰው ሞት ይጠብቀዋል።