ምሳሌ 4:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጥበብን አክብራት፤ እርስዋም ከፍ ከፍ ታደርግሃለች፤ አጥብቀህም ብትይዛት፥ ክብርን ትሰጥሃለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክብርን ስጣት፤ ከፍ ከፍ ታደርግሃለች፤ ዕቀፋት፤ ታከብርሃለች፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከፍ ከፍ አድርጋት፥ እርሷም ከፍ ከፍ ታደርግሃለች፥ ብታቅፋትም ታከብርሃለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጠብቃት፥ እርስዋም ከፍ ከፍ ታደርግሃለች፤ አክብራት፥ እርስዋም ታቅፍሃለች። |
በዚያን ጊዜ ጠቢባን እንደ ሰማይ ብርሃን ያንጸባርቃሉ፤ ብዙ ሰዎችን በማስተማር ከክፉ መንገድ ወደ ደግ ሥራ የመለሱ ሁሉ ለዘለዓለም እንደ ሰማይ ከዋክብት ያበራሉ።”
ስለዚህ የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘የአንተ ቤተሰብና የቀድሞ አባትህ ቤተሰብ ለዘለዓለም ያገለግሉኝ ዘንድ ቃል ገብቼ ነበር፤ አሁን ግን እንዲህ አይሆንም፤ የሚያከብሩኝን አከብራለሁ የሚንቁኝም ይናቃሉ።