ምሳሌ 4:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግሮችህ በቀና መንገድ ላይ ይራመዱ። መንገድህም ሁሉ ይቃናልሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የእግርህን ጐዳና አስተካክል፤ የጸናውን መንገድ ብቻ ያዝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእግርህን መንገድ አቅና፥ አካሄድህም ሁሉ ይጽና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለእግርህ ቀና መሄጃ ሥራ፥ መንገዶችህንም አቅና። |
በዚህ ዐይነት ጌታችን ኢየሱስ ከቅዱሳኑ ሁሉ ጋር በሚመጣበት ጊዜ በአምላካችንና በአባታችን ፊት ልባችሁ ነቀፋ የሌለበትና ቅዱስ እንዲሆን ያበረታችኋል።
ለጥቂት ጊዜ መከራ ከተቀበላችሁ በኋላ በክርስቶስ ወደ ዘለዓለም ክብር የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ እርሱ ራሱ ከተቀበላችሁት መከራ ያድናችኋል፤ ይደግፋችኋል፤ ያጸናችኋል፤ ይመሠርታችኋልም።