ምሳሌ 4:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የክፉዎች መንገድ ግን እንደ ድቅድቅ ጨለማ ነው፤ ይወድቃሉ፤ የመውደቂያቸው ምክንያት ምን እንደ ሆነ አያውቁም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የክፉዎች መንገድ ግን እንደ ድቅድቅ ጨለማ ነው፤ ምን እንደሚያሰናክላቸውም አያውቁም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የክፋት መንገድ እንደ ጨለማ ነው፥ እንዴት እንደሚሰናከሉም አያውቁም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኃጥኣን መንገዶች ግን ጨለማ ናቸው። እንዴት እንደሚሰናከሉም አያውቁም። |
ጨለማን አምጥቶ በተራራዎች ከመሰናከላችሁ በፊት ተስፋ ያደረጋችኹትን ብርሃን ወደ ድቅድቅ ጨለማና ወደ ጥልቅ ጭጋግ ከመለወጡ በፊት አምላካችሁን እግዚአብሔርን አክብሩ።
ስለዚህም መንገዳቸው የሚያዳልጥ መሬት ይሆናል፤ በጨለማም ሲራመዱ መንገዳቸውን ስተው ይወድቃሉ፤ በሚቀጡበትም ቀን ክፉ ነገርን አመጣባቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።
ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፦ “አሁን ለጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር ብርሃን አለ፤ ጨለማ እንዳይደርስባችሁ ብርሃን ሳለላችሁ ተመላለሱ፤ በጨለማ የሚመላለስ ወዴት እንደሚሄድ አያውቅም።