ምሳሌ 3:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን ብታደርግ ለሰውነትህ ጤንነትን፥ ለአጥንቶችህም ጥንካሬን ታገኛለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም ለሰውነትህ ጤንነትን፣ ለዐጥንትህም ልምላሜን ያመጣልሃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም ለሥጋህ ፈውስ ይሆንልሃል፥ ለአጥንትህም መታደስ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህም ለሥጋህ ፈውስ፥ ለአጥንትህም ጠገን ይሆንልሃል። |
ከዚህም የተነሣ ከእግር ጥፍር እስከ ራስ ጠጒር ድረስ ጤናማ የሆነ የአካል ክፍል የላችሁም፤ ቊስልና እባጭ መግልም የሞላበት ሆኖአል፤ ይህም ቊስላችሁ አልፈረጠም፤ አልታሰረም፤ ወይም በዘይት አለሰለሰም።
ይህም ሲፈጸም በምታዩበት ጊዜ ሐሴት ታደርጋላችሁ፤ ሰውነታችሁም እንደ ሣር ይለመልማል፤ የእግዚአብሔር ኀይል ከአገልጋዮቹ ጋር፥ ቊጣው ግን በሚጠሉት ላይ እንደሚሆን ይታወቃል።”