ጒዳት ላደርስብህ እችል ነበር፤ ነገር ግን ባለፈው ሌሊት የአባትህ አምላክ ‘ያዕቆብን፥ ክፉም ሆነ ደግ አንድ ቃል እንዳትናገረው’ ብሎ አስጠነቀቀኝ፤
ምሳሌ 3:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ርዳታ እንድታደርግለት ለሚገባው ሰው ዐቅምህ በሚፈቅድልህ መጠን በጎ ነገር ከማድረግ አትቈጠብ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማድረግ እየቻልህ ለሚገባቸው መልካም ነገር ከማድረግ አትቈጠብ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልታደርግለት የሚቻልህ ሲሆን፥ ለተቸገረው ሰው በጎ ነገርን ከማድረግ አትቆጠብ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለተቸገረው ሰው በጎ ነገር ማድረግን ቸል አትበል፥ በእጅህ ያለውን ያህል ርዳው። |
ጒዳት ላደርስብህ እችል ነበር፤ ነገር ግን ባለፈው ሌሊት የአባትህ አምላክ ‘ያዕቆብን፥ ክፉም ሆነ ደግ አንድ ቃል እንዳትናገረው’ ብሎ አስጠነቀቀኝ፤
ክፉ ሥራ ለመሥራት ለሚያቅዱና በመኝታቸው ሳሉ ተንኰል ለሚያውጠነጥኑ ወዮላቸው! ያን ለማድረግ ሥልጣን ስላላቸው ሌሊቱ ሲነጋ ዕቅዳቸውን በሥራ ላይ ያውሉታል።
እንግዲህ ለበላይ ባለሥልጣን ሊደረግ የሚገባውን ሁሉ አድርጉ፤ ግብር ለሚገባው ግብርን፥ ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን ክፈሉ፤ መፈራት ለሚገባው መፈራትን፥ ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ።
ክርስቶስ ከዐመፃ ሁሉ ሊያድነንና መልካም ሥራ ለመሥራት ትጉሆችና ለእርሱ የተለየን ንጹሕ ሕዝብ እንድንሆን ያነጻን ዘንድ ስለ እኛ ራሱን አሳልፎ ሰጠ።
ይሁን እንጂ በእርሻችሁ ሲያጭዱ ለዋሉት ሠራተኞች ዋጋቸውን ስላልከፈላችሁ እነሆ፥ የተቃውሞ ጩኸታቸው ይሰማል፤ የመከር ሰብሳቢዎቹንም ጩኸት የሠራዊት ጌታ ሰምቶአል።