እግዚአብሔር በጥበብ ምድርን መሠረተ፤ በማስተዋልም ሰማያትን አጸና።
እግዚአብሔር በጥበብ ምድርን መሠረተ፤ በማስተዋል ሰማያትን በየስፍራቸው አጸና፤
ጌታ በጥበብ ምድርን መሠረተ፥ በማስተዋልም ሰማያትን አጸና።
እግዚአብሔር በጥበብ ምድርን መሠረተ፥ በማስተዋልም ሰማያትን አዘጋጀ።
ለመሆኑ ዓለምን ስፈጥር አንተ በዚያ ነበርክን? የምታውቅና የምታስተውል ከሆነ እስቲ ንገረኝ።
እግዚአብሔር ሆይ! አንተ ብዙ ነገሮችን ፈጥረሃል፤ ሁሉንም በጥበብ አድርገሃል፤ ምድር አንተ በፈጠርካቸው ነገሮች ተሞልታለች።
በጥበቡ ሰማያትን ፈጠረ፤ ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው።
“እግዚአብሔር ከሁሉ በፊት ፈጠረኝ፤ ከጥንት ጀምሮ የሥራው ተቀዳሚ አደረገኝ።
እግዚአብሔር በኀይሉ ምድርን ሠራ፤ በጥበቡም ዓለምን ፈጠረ፤ በማስተዋሉም ሰማያትን ዘረጋ፤
እግዚአብሔር በኀይሉ ምድርን፥ በጥበቡም ዓለምን ፈጠረ፤ በማስተዋሉም ሰማያትን ዘረጋ፤
ሁሉ ነገር በእርሱ ተፈጠረ፤ ከተፈጠረው ሁሉ፥ አንድም ነገር ያለ እርሱ የተፈጠረ የለም።