ጥበብ ከውድ ዕንቊ ትከብራለች፤ አንተ ለማግኘት ከምትመኛቸው ነገሮች ሁሉ እርስዋን የሚወዳደራት ከቶ የለም።
ከቀይ ዕንቍ ይበልጥ ውድ ናት፤ አንተ ከምትመኘውም ሁሉ የሚስተካከላት የለም።
ከውድ ዕንቁም ትከብራለች፥ ከምትመኘው ነገር አንዳችም አይተካከላትም።
ዋጋው ብዙ ከሆነ ዕንቍም የከበረች ናት። ክፉ ነገር አይቃወማትም፥ ለሚቀርቧትም መልካም ናት። ክብርም ሁሉ አይተካከላትም።
የከበሩ ዛጐልና አልማዝ ከጥበብ ጋር አይወዳደሩም። የጥበብ ዋጋ ከሉልም በላይ ነው።
ዘለዓለማዊው ፍቅርህ ከሕይወት እንኳ የሚሻል ስለ ሆነ አመሰግንሃለሁ።
ዕውቀት የተሞላበት ንግግር፥ ከወርቅና ከከበረ ዕንቊ ይበልጥ የተወደደ ነው።
ጠባየ መልካምን ሚስት ማን ሊያገኛት ይችላል? እርስዋ ከዕንቊ ይልቅ የከበረች ናት።
ከብር ይልቅ ምክሬን ምረጡ፤ ከንጹሕ ወርቅ ይልቅ ዕውቀትን ምረጡ።
“እኔ ጥበብ፥ ከዕንቊ የምበልጥ ስለ ሆንኩ ምንም ነገር ብትመኙ ከእኔ የሚወዳደር አንድም ነገር የለም።
ጥበብን ማግኘት ርስትን ከመውረስ የተሻለ ስለ ሆነ በዚህ ዓለም የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ጠቢባን መሆን ይገባቸዋል፤
የአሁኑ ጊዜ መከራ ወደፊት ለእኛ ከሚገለጥልን ክብር ጋር ቢመዛዘን በምንም ሊተካከል እንደማይችል አድርጌ እቈጥረዋለሁ።