ልጄ ሆይ! የእግዚአብሔርን ተግሣጽ አትናቅ፤ በሚገሥጽህም ጊዜ አትመረር።
ልጄ ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ተግሣጽ አትናቅ፤ በዘለፋውም አትመረር፤
ልጄ ሆይ፥ የጌታን ተግሣጽ አትናቅ፥ በገሠጸህም ጊዜ አትመረር።
ልጄ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ተግሣጽ ቸል አትበል፥ በመገሠጹም ከእርሱ የተነሣ አትመረር።
አሁን ግን ችግር ስለ መጣብህ ተስፋ ቢስ ሆነሃል፤ ችግሩም ስለ በረታብህ ተስፋ ቈርጠሃል።
“እግዚአብሔር የሚገሥጸው ሰው የተባረከ ነው! ስለዚህ የልዑል እግዚአብሔርን ተግሣጽ አትናቅ።
እግዚአብሔር ሆይ! አንተ የምትገሥጸውና ሕግህንም የምታስተምረው ሰው እንዴት የተባረከ ነው!
መከራ በሚደርስብህ ጊዜ መጽናት የማትችል ከሆንክ ምንም ብርታት የለህም ማለት ነው።
ነገር ግን በኋላ ከዓለም ጋር እንዳንኰነን አሁን ፈርዶ ጌታ ይገሥጸናል።
እግዚአብሔር በምሕረቱ ይህን አገልግሎት ስለ ሰጠን ተስፋ አንቈርጥም።
አባት ልጆቹን እንደሚገሥጽ አምላክህ እግዚአብሔርም አንተን የሚገሥጽህ መሆኑን አስተውል።
እንግዲህ ሳትሰለቹና ተስፋ ሳትቈርጡ ይህን ሁሉ የኃጢአተኞችን ተቃውሞ የታገሠውን ኢየሱስን ተመልከቱ።
እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ፤ እቀጣቸዋለሁም፤ ስለዚህ ትጋ፤ ንስሓም ግባ፤