Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መዝሙር 94:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 እግዚአብሔር ሆይ! አንተ የምትገሥጸውና ሕግህንም የምታስተምረው ሰው እንዴት የተባረከ ነው!

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ብፁዕ ነው፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ የምትገሥጸው፣ ከሕግህም የምታስተምረው ሰው፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12-13 ለክፉ ሰው ጉድጓድ እስኪቈፈር ድረስ ከአስከፊ ዘመናት ይወገድ ዘንድ፥ አቤቱ፥ አንተ የገሠጽኸው ሕግህንም ያስተማርኸው ሰው ብፁዕ ነው።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 94:12
10 Referencias Cruzadas  

“እግዚአብሔር የሚገሥጸው ሰው የተባረከ ነው! ስለዚህ የልዑል እግዚአብሔርን ተግሣጽ አትናቅ።


ነገር ግን በኋላ ከዓለም ጋር እንዳንኰነን አሁን ፈርዶ ጌታ ይገሥጸናል።


እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ፤ እቀጣቸዋለሁም፤ ስለዚህ ትጋ፤ ንስሓም ግባ፤


ሕግህን እንድማር ስላደረገኝ መቀጣቴ መልካም ሆነልኝ።


አንተ እኔን ከመቅጣትህ በፊት እሳሳት ነበር፤ አሁን ግን ለቃልህ እታዘዛለሁ።


አባት ልጆቹን እንደሚገሥጽ አምላክህ እግዚአብሔርም አንተን የሚገሥጽህ መሆኑን አስተውል።


እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብ ነው፤ እርሱ ከተማይቱን እንዲህ ይላል፦ “እናንተ በከተማይቱ የተሰበሰባችሁ ሰዎች አድምጡ!


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios