ይህም ሁሉ ሆኖ የእስራኤል ንጉሥ ኢዮርብዓም ከሚያደርገው ክፉ ነገር ሁሉ አልተመለሰም፤ ይልቁንም እርሱ በሠራቸው መሠዊያዎች የሚያገለግሉ ከሌዊ ዘር ውጪ ከሆኑ ቤተሰቦች መምረጡን ቀጥሎ ካህን ለመሆን ከፈለገ ማንኛውንም ሰው ይሾመው ነበር፤
ምሳሌ 27:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እህል በሙቀጫ ውስጥ በዘነዘና እንደሚወቀጥ ሞኝንም ለመሞት እስኪቃረብ ድረስ ብትመታው እንኳ ሞኝነቱን ከእርሱ ማስወገድ አትችልም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቂልን በሙቀጫ ብትወቅጠው፣ እንደ እህልም በዘነዘና ብታደቅቀው፣ ቂልነቱን ልታስወግድለት አትችልም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰነፍን በሙቀጫ ውስጥ ከእህል ጋር በዘነዘና ብትወቅጠው፥ ሞኝነቱ ከእርሱ አይርቅም። |
ይህም ሁሉ ሆኖ የእስራኤል ንጉሥ ኢዮርብዓም ከሚያደርገው ክፉ ነገር ሁሉ አልተመለሰም፤ ይልቁንም እርሱ በሠራቸው መሠዊያዎች የሚያገለግሉ ከሌዊ ዘር ውጪ ከሆኑ ቤተሰቦች መምረጡን ቀጥሎ ካህን ለመሆን ከፈለገ ማንኛውንም ሰው ይሾመው ነበር፤
በዚያኑ ሌሊት ንጉሡና መኳንንቱ፥ መላውም የግብጽ ሕዝብ ሁሉ ከእንቅልፋቸው ነቁ፤ ወንድ ልጅ ያልሞተበት አንድ ቤት እንኳ ስላልነበረ በግብጽ ምድር ሁሉ ታላቅ የለቅሶ ጩኸት አስተጋባ።
የግብጽ ንጉሥ ሕዝቡ ማምለጣቸው በተነገረው ጊዜ እርሱና መኳንንቱ ሐሳባቸውን ለውጠው “ይህ ያደረግነው ነገር ምንድን ነው? እስራኤላውያን አምልጠው እንዲሄዱ ስንፈቅድ አገልጋዮቻችንን ሁሉ ማጣታችን አይደለምን?” አሉ።
እንዲሁም “ተደብድቤአለሁ፤ ነገር ግን አልተጐዳሁም፤ ተመትቼአለሁ፤ ሕመሙ ግን አልተሰማኝም፤ መቼ ነው የምነቃው? ሌላ ተጨማሪ መጠጥ የምጠጣው መቼ ይሆን?” ትላለህ።
ኢትዮጵያዊ መልኩን፥ ነብርም ዝንጒርጒርነቱን መለወጥ አይችልም፤ እንዲሁም እናንተ ክፉ ነገር ማድረግን ስለ ለመዳችሁ ደግ ሥራ መሥራት አይሆንላችሁም።
እግዚአብሔር ሆይ ዐይኖችህ እውነትን የሚመለከቱ አይደሉምን? አንተ ቀሠፍሃቸው፤ እነርሱ ግን ከምንም አልቈጠሩትም፤ አደቀቅሃቸው፤ እነርሱ ከስሕተታቸው መማር እምቢ አሉ፤ እልኸኝነትን አበዙ እንጂ፥ ከኃጢአታቸው መመለስ አልፈለጉም።
ሳኦል ይህን በሰማ ጊዜ ሌሎች መልእክተኞችን ላከ፤ እነርሱም እንደዚያው ትንቢት መናገር ቀጠሉ፤ ሳኦልም ለሦስተኛ ጊዜ ሌሎች መልእክተኞችን ቢልክ ያው ነገር በእነርሱም ላይ ተደገመ፤