ምሳሌ 23:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጥበብ የሞላበት ምክርህን ስለሚንቅብህ ለሞኝ ሰው ቁም ነገር አታጫውተው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሞኝ ጋራ አትነጋገር፤ የቃልህን ጥበብ ያንኳስሳልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሞኝ ጆሮ ምንም አትናገር፥ በቃልህ ጥበብ ያፌዛልና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሰነፍ ጆሮ አንዳች አትናገር፥ የነገርህን ጥበብ እንዳይንቅብህ። |
የተቀደሰውን ነገር ለውሾች አትስጡ፤ ዕንቋችሁንም በዐሣማዎች ፊት አትጣሉ፤ ዐሣማዎቹ ዕንቋችሁን በእግራቸው ይረግጡታል፤ ውሾቹም ተመልሰው ይነክሱአችኋል።
አይሁድ እንዲህ አሉት፦ “ጋኔን እንዳለብህ አሁን ዐወቅን፤ አብርሃም እንኳ ሞቶአል፤ ነቢያትም ሞተዋል፤ አንተ ግን ‘ቃሌን የሚጠብቅ አይሞትም’ ትላለህ፤
ኤፒኮሮሶችና እስቶይኮች የተባሉ ፈላስፎችም ወደ እርሱ እየመጡ ይከራከሩ ነበር። አንዳንዶቹ “ይህ ለፍላፊ ምን ማለት ይፈልጋል?” ሲሉ፥ ሌሎች ደግሞ “ስለ አዳዲስ አማልክት የሚናገር ይመስላል” ይሉ ነበር፤ ይህንንም ያሉበት ምክንያት ጳውሎስ የኢየሱስንና የትንሣኤውን መልካም ዜና ስላበሠረ ነው።