አገልጋዮቹንም “አምኖን ብዙ ጠጥቶ መስከሩን ተመልከቱ፤ እኔም ትእዛዝ በምሰጣችሁ ጊዜ ግደሉት፤ ይህን ትእዛዝ የሰጠኋችሁ እኔ ስለ ሆንኩ ከቶ አትፍሩ! ደፋሮች ሁኑ፤ ምንም አታመንቱ!” አላቸው።
ምሳሌ 23:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በባሕር ውስጥ ያለህና ማዕበል ከሚያንገላታት መርከብ ምሰሶ ላይ የተወዳጀህ ይመስልሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በባሕር ላይ የተኛህ፣ በመርከብ ምሰሶ ጫፍ ላይ የተጋደምህ ትመስላለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በባሕር ውስጥ እንደ ተኛ ትሆናለህ፥ በመርከብም ምሶሶ ላይ እንደ ተኛ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጥልቅ ባሕር ውስጥ እንደሚተኛ ትሆናለህ፥ በብዙ ማዕበል ውስጥም እንደሚቀዝፍ። |
አገልጋዮቹንም “አምኖን ብዙ ጠጥቶ መስከሩን ተመልከቱ፤ እኔም ትእዛዝ በምሰጣችሁ ጊዜ ግደሉት፤ ይህን ትእዛዝ የሰጠኋችሁ እኔ ስለ ሆንኩ ከቶ አትፍሩ! ደፋሮች ሁኑ፤ ምንም አታመንቱ!” አላቸው።
የሠረገላዎቹ እኩሌታ ኀላፊ የሆነ ዚምሪ ተብሎ የሚጠራ ከጦር መኰንኖቹ አንዱ በንጉሡ ላይ ዐደመ፤ አንድ ቀን ኤላ በቲርጻ ከተማ የቤተ መንግሥቱ ኀላፊ በሆነው አርጻ ተብሎ በሚጠራው ባለሟሉ ቤት ብዙ መጠጥ ጠጥቶ ሰክሮ ነበር።
እንዲሁም “ተደብድቤአለሁ፤ ነገር ግን አልተጐዳሁም፤ ተመትቼአለሁ፤ ሕመሙ ግን አልተሰማኝም፤ መቼ ነው የምነቃው? ሌላ ተጨማሪ መጠጥ የምጠጣው መቼ ይሆን?” ትላለህ።
ከእንግዲህ ወዲህ አዲስ የወይን ጠጅ በአፋችሁ ስለማትቀምሱ፥ እናንተ ሰካራሞች ከእንቅልፋችሁ ነቅታችሁ አልቅሱ፤ እናንተም የወይን ጠጅ መጠጣት የምታዘወትሩ ምርር ብላችሁ አልቅሱ።
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “በመብልና በመጠጥ ብዛት በስካርም በመባከንና ስለ ዓለማዊ ኑሮ በመጨነቅ ልባችሁ እንዳይዝል ተጠንቀቁ! አለበለዚያ ያ ቀን እንደ ወጥመድ በድንገት ይይዛችኋል።