Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ምሳሌ 31:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 “ልሙኤል ሆይ! ነገሥታት ወይን ጠጅ ይጠጡ ዘንድ፥ መሳፍንትም ጠንካራ መጠጥን ለመጠጣት ይጓጉ ዘንድ ተገቢ አይደለም።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 “ልሙኤል ሆይ፤ ነገሥታት ይህን ማድረግ የለባቸውም፤ ነገሥታት የወይን ጠጅ ሊጠጡ፣ ገዦችም የሚያሰክር መጠጥ ሊያስጐመጃቸው አይገባም፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ለነገሥታት አይገባም፥ ልሙኤል ሆይ፥ ነገሥታት የወይን ጠጅ ሊጠጡ፥ መሳፍንትም፦ ብርቱ መጠጥ ወዴት ነው? ሊሉ አይገባም፥

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 31:4
16 Referencias Cruzadas  

የሠረገላዎቹ እኩሌታ ኀላፊ የሆነ ዚምሪ ተብሎ የሚጠራ ከጦር መኰንኖቹ አንዱ በንጉሡ ላይ ዐደመ፤ አንድ ቀን ኤላ በቲርጻ ከተማ የቤተ መንግሥቱ ኀላፊ በሆነው አርጻ ተብሎ በሚጠራው ባለሟሉ ቤት ብዙ መጠጥ ጠጥቶ ሰክሮ ነበር።


ቤንሀዳድና የእርሱ የጦር ቃል ኪዳን ጓደኞቹ የሆኑ ሌሎችም ነገሥታት በድንኳኖቻቸው ውስጥ ሆነው ሲጠጡ ሳሉ የአክዓብ መልእክት ደረሰ፤ በዚህን ጊዜ ቤንሀዳድ በከተማይቱ ላይ አደጋ ለመጣል እንዲዘጋጁ ትእዛዝ ሰጠ፤ ስለዚህም እነርሱ ፈጥነው በመንቀሳቀስ ቦታ ቦታቸውን ያዙ።


ግብዣው በተጀመረ በሰባተኛው ቀን ንጉሥ አርጤክስስ በወይን ጠጅ ረክቶ ደስ ባለው ጊዜ መሁማን፥ ቢዝታ፥ ሐርቦና፥ ቢግታ፥ አባግታ፥ ዜታርና ካርካስ ተብለው የሚጠሩትን ጃንደረቦች የሆኑትን ሰባቱን የእልፍኝ አገልጋዮቹን ወደ እርሱ ጠርቶ፥


በንጉሡም ትእዛዝ ዐዋጁ ሱሳ ተብላ በምትጠራው መናገሻ ከተማ በይፋ ተገልጦ እንዲታይ ተደረገ፤ ፈጣኖች የሆኑ ሯጮችም ወደየአገሩ መልእክቱን አደረሱ፤ መናገሻ ከተማይቱ ሱሳ ታውካ ሳለች፥ ንጉሡና ሃማን በአንድነት ተቀምጠው የወይን ጠጅ ይጠጡ ነበር።


ወይን ጠጅ ፌዘኛ፥ ጠንካራ መጠጥም ጠበኛ ያደርጋሉ፤ በእነርሱ ሱስ የተጠመደ ጥበበኛ ሊሆን አይችልም።


በባሕር ውስጥ ያለህና ማዕበል ከሚያንገላታት መርከብ ምሰሶ ላይ የተወዳጀህ ይመስልሃል።


በጨዋነት ያደገ ንጉሥና ለስካር ሳይሆን ብርታትና ኀይል ለማግኘት ብቻ በተወሰነ ጊዜ የሚበሉና የሚጠጡ መሪዎች ያሉአት አገር የተባረከች ናት።


የወይን ጠጅ በመጠጣት ጀግኖች፥ የሚያሰክረውንም መጠጥ ለማደባለቅ ደፋሮች ለሆኑ ወዮላቸው!


በእርግጥ ሀብት ሰውን ያታልላል፤ ትምክሕተኛ ሰው ዕረፍት የለውም፤ እንደ መቃብር ስስታም እንደ ሞትም በቃኝ የማይል ስለ ሆነ መንግሥታትን ሁሉ ለራሱ ይወራል፤ ሕዝቦችንም ይማርካል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos