ከንዴተኛና ከቊጡ ሰው ጋር ባልንጀራ አትሁን፤
ከግልፍተኛ ጋራ ወዳጅ አትሁን፤ በቀላሉ ቱግ ከሚልም ሰው ጋራ አትወዳጅ፤
ከቁጡ ሰው ጋር ባልንጀራ አትሁን፥ ከንዴተኛም ጋር አትሂድ፥
ከቍጡ ሰው ጋር ባልንጀራ አትሁን፥ ከነዝናዛም ጓደኛ ጋር አትኑር።
ከጥበበኞች የሚወዳጅ ጥበበኛ ይሆናል። ማስተዋል ከጐደላቸው ሰዎች ጋር ጓደኛ የሚሆን ግን ይጐዳል።
ቊጣ ጭቅጭቅን ያነሣሣል፤ ትዕግሥት ግን ጠብን ያበርዳል።
ትዕቢተኛና ትምክሕተኛ ሰው ፌዘኛ ነው፤ ድርጊቱም በትዕቢት የተሞላ ነው።
ቊጡ ሰው ጠብን ያነሣሣል፤ ግልፍተኛም ብዙ በደልን ይፈጽማል።