ምሳሌ 22:21 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እውነት ምን እንደ ሆነም ያስተምሩሃል፤ “እውነትን ፈልገህ አቅርብ” ተብለህ ብትጠየቅም ትክክለኛውን መልስ ትሰጣለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለላከህ ተገቢውን መልስ ትሰጥ ዘንድ፣ እውነተኛና የታመኑ ቃሎችን እንዳስተምርህ አይደለምን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጎ ዕውቀትን ትሰማ ዘንድ፥ ለሚጠይቁህም የእውነት ቃልን ትመልስ ዘንድ ነዋሪ ቃልን አስተምርሃለሁ። |
ጌታ ክርስቶስን በልባችሁ አክብሩት፤ ለሕይወታችሁም ጌታ አድርጉት፤ በእናንተ ስላለውም ተስፋ ለሚጠይቃችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ሁልጊዜ ዝግጁዎች ሁኑ።