ምሳሌ 22:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ ሠላሳ መመሪያዎችን ጽፌልሃለሁ፤ እነርሱ ዕውቀትና መልካም ምክር የሚገኙባቸው ናቸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የምክርና የዕውቀት ቃል የሆኑ፣ መልካም ሠላሳ ትምህርቶችን አልጻፍሁልህምን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእውነትን ቃል እርግጥነት አስታውቅህ ዘንድ፥ ለሚጠይቅህም እውነትን ቃል መመለስ ይቻልህ ዘንድ፥ በምክርና በእውቀት ሠላሳ ምሳሌዎችን አልጻፍሁልህምን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለዕውቀትና ለምክር ይሆኑህ ዘንድ ሦስት ነገሮችን እነሆ ጻፍሁልህ። አንተም በልብህ ሰሌዳነት ጻፋቸው። |