ሀብታምንም ሆነ ድኻን የፈጠራቸው እግዚአብሔር ስለ ሆነ ሁለቱም በዚህ አንድ ናቸው።
ባለጠጋና ድኻ የሚጋሩት ነገር፣ እግዚአብሔር የሁላቸውም ፈጣሪ መሆኑ ነው።
ሀብታምና ድሀ ይገናኛሉ፥ ሁለቱንም የፈጠራቸው ጌታ ነው።
ባለ ጠጋና ድሃ በአንድነት ተገናኙ፤ ሁለቱንም እግዚአብሔር ፈጠራቸው።
በማሕፀን ውስጥ እኔን የፈጠረ አገልጋዮቼንስ የፈጠረ አይደለምን? ሁላችንንስ በማሕፀን ውስጥ የሠራ፥ እርሱ አይደለምን?
ሁሉም የእጁ ሥራዎች ስለ ሆኑ፤ እርሱ ለመኳንንቱ አያደላም ባለጸጋውን ከድኻው አይለይም።
ድኾችን ማስጨነቅ ፈጣሪን መናቅ ነው፤ ለድኾች ቸርነትን ማድረግ ግን እግዚአብሔርን እንደ ማክበር ይቈጠራል።
ለድኻና እርሱንም ለሚጨቊነው ሰው የዐይን ብርሃን የሚሰጠው እግዚአብሔር ስለ ሆነ በብርሃን አጠቃቀም ሁለቱም እኩል ናቸው።
ዐይን እጅን “አንተ አታስፈልገኝም!” ሊለው አይችልም፤ ራስም እግርን “አንተ አታስፈልገኝም!” ሊለው አይችልም፤
እግዚአብሔር ያደኸያል፤ ያበለጽጋልም፤ ያዋርዳል፤ ከፍ፥ ከፍም ያደርጋል።