ከጨቅጫቃ ሚስት ጋር በአንድ ቤት ከመኖር ይልቅ በጣራ ማእዘን ላይ መኖር ይሻላል።
ከጨቅጫቃ ሚስት ጋራ በአንድ ቤት ከመኖር፣ በጣራ ማእዘን ላይ መኖር ይሻላል።
ከጠበኛ ሴት ጋር በአንድ ቤት ከመቀመጥ በውጪ በቤት ማዕዘን ላይ መቀመጥ ይሻላል።
ከነዝናዛ ሴት ጋር በተለሰነ ቤት ከመቀመጥ ይልቅ፥ ከቤት ውጭ በማዕዘን ላይ መቀመጥ ይሻላል።
አስተዋይ ሴት ለባልዋ ዘውድ ናት፤ ባልዋን የምታሳፍር ሴት ግን አጥንትን እንደሚያደቅ በሽታ ናት። እንደሚጐዳ ነቀርሳ በሽታ ትሆንበታለች።
ጥላቻ ባለበት ስፍራ ጮማ ሥጋ ከመብላት ፍቅር ባለበት ስፍራ ጎመን መብላት ይሻላል።
ጥልና ክርክር በበዛበት ቤት በታላቅ ግብዣ ላይ ከመገኘት ይልቅ ሰላም ባለበት ቤት ደረቅ የዳቦ ቊራሽ መመገብ ይሻላል።
ሞኝ ልጅ አባቱን ወደ ጥፋት ያደርሳል፤ ጨቅጫቃ ሚስትም እንደማያቋርጥ ዝናብ አሰልቺ ናት።
ዐመፀኞች ዘወትር ክፋትን ማድረግ ይወዳሉ፤ ለማንም ሰው ርኅራኄ የላቸውም።
ከጨቅጫቃና ከነዝናዛ ሚስት ጋር አብሮ ከመኖር በምድረ በዳ መኖር ይሻላል።
ኃጢአተኞች በጠማማ መንገድ መሄድ ይወዳሉ፤ ልበ ንጹሖች ግን መልካም የሆነውን ነገር ያደርጋሉ።