መሬቱን በወቅቱ የማያርስ ሰነፍ ገበሬ በመከር ጊዜ የሚሰበስበው ምርት አይኖረውም።
ሰነፍ ሰው በወቅቱ አያርስም፤ ስለዚህ በመከር ወራት ይፈልጋል፤ አንዳችም አያገኝም።
ታካች ሰው በብርድ ምክንያት አያርስም፥ ስለዚህ በመከር ይለምናል፥ ምንም አያገኝም።
ታካች ሰው ሲያሽሟጥጡት አያፍርም፤ ስለዚህ በመከር ጊዜ ይለምናል፥ የሚሰጠውም የለም። በክምሩ እያለ ስንዴ የሚበደር እንደዚሁ ነው።
ስንፍና ያደኸያል፤ ተግቶ መሥራት ግን ያበለጽጋል፤
ሰነፍ አንድ ነገር ለማግኘት አጥብቆ ይመኛል፤ ይሁን እንጂ አያገኝም፤ ትጉህ ሠራተኛ ግን የሚፈልገውን ሁሉ ያገኛል።
ስንፍና እንቅልፍን ያስከትላል፤ ስለዚህም ሰነፍ ሰው ይራባል።
አንዳንድ ሰዎች በጣም ሰነፎች ናቸው፤ ሌላው ቀርቶ በወጥ ያጠቀሱትን እንጀራ መጒረስ ይታክታቸዋል።
የሰው ሐሳብ በጥልቅ ጒድጓድ ውስጥ እንዳለ ውሃ ነው፤ ይሁን እንጂ ማስተዋል ያለው ሰው ይቀዳዋል።
መሥራት የማይፈልግ ሰነፍ ሰው ራሱን የገደለ ያኽል ይቈጠራል።
ነገር ግን ገና ተኝተህ ሳለህ ድኽነትና ማጣት የጦር መሣሪያ እንደ ታጠቀ ወንበዴ በድንገት እንደሚደርሱብህ ዕወቅ።
አንተ ሰነፍ ወደ ጒንዳን ሄደህ መንገድዋን ተመልክተህ ጥበብን ቅሰም።
ነፋስን የሚጠብቅ አይዘራም፤ ደመናን የሚመለከት አያጭድም።