ምሳሌ 2:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን ሁሉ ብታደርግ እግዚአብሔርን መፍራት ምን እንደ ሆነ ታውቃለህ፤ የአምላክንም ዕውቀት ታገኛለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜ ፈሪሀ እግዚአብሔርን ትረዳለህ፤ አምላክንም ማወቅ ታገኛለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዚያን ጊዜ ጌታን መፍራትን ትገነዘባለህ፥ የአምላክንም እውቀት ታገኛለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን መፍራት ታውቃለህ፥ አምላክን ማወቅንም ታገኛለህ። |
እኔ እግዚአብሔር መሆኔን እንዲያውቁ አደርጋቸዋለሁ። ከዚያ በኋላም በሙሉ ልባቸው ወደ እኔ ስለሚመለሱ፥ እነርሱ ሕዝቤ ይሆናሉ፤ እኔም አምላካቸው እሆናለሁ።
ከእንግዲህ ወዲህ ‘እግዚአብሔርን ዕወቅ’ ብሎ ባልንጀራውንም ሆነ ወንድሙን የሚያስተምር ማንም አይኖርም፤ ከትልቁ ጀምሮ እስከ ትንሹ ሁሉም ያውቁኛል፤ በደላቸውን ይቅር እልላቸዋለሁ፤ ኃጢአታቸውንም አላስታውስባቸውም፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
አንድ ሰው መመካት ካለበት በምድር ላይ ምሕረትን፥ ትክክለኛ ፍርድንና እውነትን የማስገኝ እኔ አምላክ መሆኔን በመረዳት ይመካ፤ እኔም ደስ የሚያሰኘኝ ይኸው ነው፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
ኑ፤ እግዚአብሔርን እንወቅ፤ ሳናወላውልም እንከተለው፤ እርሱም እንደ ንጋት ብርሃንና ምድርን እንደሚያረካ የበልግ ዝናም በእርግጥ ወደ እኛ ይመጣል።”
አባቴ ሁሉን ነገር ሰጥቶኛል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ ማንም የለም። እንዲሁም ከወልድ በቀር አብን የሚያውቅ የለም፤ ማንም ወልድ ካልገለጠለት በቀር አብን ሊያውቅ አይችልም።
“ሁሉ ነገር ከአባቴ ተሰጥቶኛል፤ ወልድ ማን መሆኑን ከአብ በቀር ማንም የሚያውቅ የለም፤ እንዲሁም አብ ማን መሆኑን ከወልድ በቀር ወይም ወልድ ሊገልጥለት ከሚፈቅድለት ሰው በቀር ሌላ ማንም የሚያውቅ የለም።”
የእግዚአብሔር ልጅ እንደ መጣና እውነተኛውን አምላክ እንድናውቅ አስተዋይ ልቡና እንደ ሰጠን እናውቃለን በልጁም በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከእርሱ ከእውነተኛው አምላክ ጋር ኅብረት አለን። ኢየሱስ ክርስቶስ እውነተኛው አምላክና የዘለዓለም ሕይወት ነው።