ምሳሌ 2:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ የመልካም ሰዎችን ምሳሌነት ልትከተልና የደጋግ ሰዎችንም አካሄድ ልትጠብቅ ይገባሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንተም በደጋግ ሰዎች ጐዳና ትሄዳለህ፤ የጻድቃንንም መንገድ ይዘህ ትጓዛለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተም በመልካም ሰዎች መንገድ እንድትሄድ የጻድቃንንም ጎዳና እንድትጠብቅ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቀና መንገዶችን ቢሄዱ ለስላሳ የጽድቅ መንገዶችን ባገኙ ነበር። |
እግዚአብሔር ለሕዝቡ እንዲህ ይላል፦ “በየጐዳናው ቆማችሁ ተመልከቱ፤ ጥንታዊና መልካም የሆነችው መንገድ የትኛዋ እንደ ሆነች ጠይቃችሁ ተረዱ፤ ባገኛችኋትም ጊዜ በእርስዋ ሂዱ፤ በሰላምም ትኖራላችሁ።” ሕዝቡ ግን “በእርስዋ አንሄድም!” አሉ።
ወዳጄ ሆይ! ደጉን ምሰል እንጂ ክፉውን አትምሰል። ደግ ሥራ የሚሠራ ሁሉ የእግዚአብሔር ነው። ክፉ ሥራ የሚሠራ ግን እግዚአብሔርን አላየውም።