ምሳሌ 19:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የንጉሥ ቊጣ እንደ አንበሳ ጩኸት አስፈሪ ነው፤ ከንጉሥ ዘንድ የሚገኝ ሞገስ ግን ሣርን እንደሚያለመልም ጠል ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የንጉሥ ቍጣ እንደ አንበሳ ግሣት ነው፤ በፊቱ ሞገስ ማግኘትም በሣር ላይ እንዳለ ጠል ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ አንበሳ ግሣት የንጉሥ ቁጣ ነው፥ ሞገሱም በመስክ ላይ እንዳለ ጠል ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የንጉሥ ቍጣ እንደ አንበሳ ግሣት ነው፥ ሞገሱም በመስክ ላይ እንዳለ ጠል ነው። |
ነገር ግን ይህን የንጉሡን ትእዛዝ ለንግሥት አስጢን በነገሩአት ጊዜ ወደ ንጉሡ ፊት ለመቅረብ እምቢ አለች፤ ይህም ሁኔታ ንጉሡን እጅግ አስቈጣው።
ምሕረትም ለመለመን አስቦ ንግሥት አስቴር በተቀመጠችበት ድንክ አልጋ ላይ በግንባሩ ተደፋ፤ ንጉሡም ከአትክልቱ ቦታ ተመልሶ ወደ ክፍሉ በገባ ጊዜ ይህን በማየቱ እጅግ ተቈጥቶ “ይህ ሰው በገዛ ቤተ መንግሥቴ ዐይኔ እያየ ንግሥቲቱን ሊደፍር ይፈልጋል እንዴ?” ሲል ጮኸበት። ንጉሡም ገና ይህን እንደ ተናገረ ወዲያውኑ ጃንደረቦቹ የሃማንን ፊት ሸፈኑ።
እግዚአብሔር እንዲህ ብሎኛል፦ “በቀትር ጊዜ በጸጥታ እንደምታበራ ፀሐይ፥ በመከርም ወራት በሞቃት ሌሊት እንደሚታይ ጤዛ ከሰማያዊ መኖሪያዬ ጸጥ ባለ መንፈስ ቊልቊል እመለከታለሁ።
ከገናናነቱም የተነሣ በልዩ ልዩ አገሮች የሚኖሩ ሕዝቦችና ልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩ ነገዶች ሁሉ በፊቱ በፍርሃት ይንቀጠቀጡ ነበር፤ የፈለገውን መግደልና የፈለገውን ማዳን፥ የፈለገውን መሾምና ያልፈለገውን መሻር ይችል ነበር።
ከዚህም በኋላ ዳንኤልን የከሰሱት ሰዎች ተይዘው እንዲመጡ ንጉሡ አዘዘ፤ እነርሱም ተይዘው ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋር በአንበሶች ጒድጓድ ውስጥ እንዲጣሉ አደረገ፤ ገና ወደ ጒድጓዱ አዘቅት ሳይደርሱም አንበሶቹ ቦጫጨቋቸው፤ አጥንቶቻቸውንም ሁሉ ሰባበሩ።
ከሞት የተረፉትም የእስራኤል ሕዝብ በብዙ ሕዝቦች መካከል እግዚአብሔር እንደሚልከው ጠልና በሣር እንደሚወርድ ካፊያ ይሆናሉ፤ ተማምነው የሚጠባበቁት ሰውን ሳይሆን እግዚአብሔርን ብቻ ይሆናል።