ምሳሌ 17:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አስተዋይ ሰው ወደ ጥበብ ያዞራል፤ የሞኝ ዐይኖች ግን በብዙ አቅጣጫ ይባዝናሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አስተዋይ ሰው ጥበብን ከፊቱ አይለያትም፤ የሞኝ ዐይኖች ግን እስከ ምድር ዳርቻ ይንከራተታሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአስተዋይ ፊት ጥበብ ትኖራለች፥ የሰነፍ ዐይን ግን በምድር ዳርቻ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የብልህ ሰው ፊት ዐዋቂ ነው፤ የአላዋቂ ሰው ዐይኖች ግን በምድር ዳርቻ ናቸው። |
ጥበበኞች ሰዎች መነሻና መድረሻቸውን ያውቃሉ፤ ሞኞች ግን ይህን ሁሉ አያውቁም፤” ይሁን እንጂ ጥበበኛም ሆነ ሞኝ ሁለቱም የሚኖራቸው ዕድል አንድ ዐይነት መሆኑን ተረዳሁ።