አካዝያስ ኢዮራምን ሊጠይቅ የሄደው እግዚአብሔር ይህ ጒብኝት የአካዝያስ መጥፊያ እንዲሆን ስለ ፈቀደ ነው፤ አካዝያስ በዚያ በነበረበት ጊዜ እርሱና ኢዮራም የአክዓብን ሥርወ መንግሥት ለማጥፋት እግዚአብሔር የመረጠውን የኒምሺ ልጅ ኢዩን ለመቀበል ወጡ፤
ምሳሌ 16:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰው ዕቅድ ያወጣል፤ ነገር ግን ዕቅዱ ከግቡ የሚደርሰው በእግዚአብሔር ርዳታ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰው በልቡ መንገዱን ያቅዳል፤ እግዚአብሔር ግን ርምጃውን ይወስንለታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰው ልብ መንገዱን ያዘጋጃል፥ ጌታ ግን አካሄዱን ያቀናለታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኃጥእ ለክፉ ቀን ይጠበቃል። |
አካዝያስ ኢዮራምን ሊጠይቅ የሄደው እግዚአብሔር ይህ ጒብኝት የአካዝያስ መጥፊያ እንዲሆን ስለ ፈቀደ ነው፤ አካዝያስ በዚያ በነበረበት ጊዜ እርሱና ኢዮራም የአክዓብን ሥርወ መንግሥት ለማጥፋት እግዚአብሔር የመረጠውን የኒምሺ ልጅ ኢዩን ለመቀበል ወጡ፤
በመጨረሻ የሚሆነውን ነገር ከመጀመሪያው ጀምሬ ተናግሬአለሁ፤ ወደፊት ምን እንደሚሆን ከጥንት ጀምሬ ገልጬአለሁ፤ ዓላማዬ የጸና ይሆናል፤ የምፈቅደውንም አደርጋለሁ።
“ነገ በዚህ ሰዓት ከብንያም አገር አንድ ሰው እልክልሃለሁ፤ ጩኸታቸው ወደ እኔ ስለ ደረሰ ወደ ሕዝቤ ተመልክቼአለሁና ከፍልስጥኤማውያን ጭቈና ሕዝቤን ስለሚያድን በሕዝቤ በእስራኤል ላይ መሪ አድርገህ ቀባው።”