የሞኝ ቊጣ ወዲያው ይታወቃል፤ ብልኅ ሰው ግን በእርሱ ላይ የተሰነዘረውን ስድብ ችላ ይላል።
ቂል ሰው ቍጣው ወዲያውኑ ይታወቅበታል፤ አስተዋይ ሰው ግን ስድብን ንቆ ይተዋል።
የሰነፍ ቁጣ ቶሎ ይታወቃል፥ ብልህ ሰው ግን ነውርን ይሰውራል።
ሰነፍ ቍጣውን በየቀኑ ይናገራል፤ ብልህ ሰው ግን ነውርን ይሰውራል።
ቊጣ ሞኝን ይገድለዋል፤ ቅናትም ሰውን ያጠፋል።
ጥላቻ ሁከትን ያነሣሣል፤ ፍቅር ግን በደልን ሁሉ አይታ በይቅርታ ታልፋለች።
እውነትን የሚናገር ሁሉ የታመነ ምስክርነትን ይሰጣል፤ ሐሰተኛ ምስክር ግን ሰውን ያታልላል።
የአስተዋይ ሰው ልብ ጥበብን የተሞላ ነው፤ በሞኞች ልብ ግን ጥበብ አትታወቅም።
ጥበብን ገንዘብ ላደረጋት የሕይወት ምንጭ ናት፤ ሞኞች ግን በሞኝነታቸው ይቀጣሉ።
የበደለን ሰው ይቅር የሚል ወዳጅነትን ያጸናል፤ በደልን መላልሶ የሚናገር ሰው ግን የቅርብ ወዳጆቹን ያጣል።
ቊጣህን መቈጣጠር ባትችል መከላከያ አጥር እንደሌላትና ለጠላት ተጋልጣ እንደምትገኝ ከተማ ትሆናለህ።
ድንጋይና አሸዋ ከባድ ናቸው፤ ሞኝ ሰው የሚያነሣሣው ቊጣ ግን ከሁለቱም ይከብዳል።
ሞኝ ሰው የቊጣ ስሜቱን ይገልጣል፤ ጥበበኛ ሰው ግን ቊጣውን በትዕግሥት ይገታል።
የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ይህን አትርሱ፤ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ፥ ለመናገርና ለቊጣም የዘገየ ይሁን።