ምሳሌ 12:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዕውቀትን የሚወድ ሰው ከስሕተት መታረምን ይወዳል፤ ተግሣጽን የሚጠላ ግን ጅል ሰው ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ተግሣጽን የሚወድድ ዕውቀትን ይወድዳል፤ መታረምን የሚጠላ ግን ደነዝ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተግሣጽን የሚወድድ እውቀትን ይወድዳል፥ እርማትን የሚጠላ ግን ሞኝ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተግሣጽን የሚወድድ ዕውቀትን ይወድዳል፤ ተግሣጽን የሚጠላ ግን ሰነፍ ነው። |
ደግ ሰው በቅንነት መንፈስ ሊቀጣኝና ሊገሥጸኝ ይችላል፤ ከክፉ ሰዎች ግን ክብርን እንኳ አልቀበልም፤ ዘወትርም ክፉ ሥራቸውን በመቃወም እጸልያለሁ።
እንዲገቱ ለማድረግ በልባብና በልጓም እንደሚመሩት እንደ ፈረስና እንደ በቅሎ የማይገባችሁ አትሁኑ። እንደዚያ ካላደረጋችሁ ፈረስና በቅሎ ወደ እናንተ አይቀርቡም።
እንዲሁም የሚጠፉትን ሰዎች የሚያታልሉት ማናቸውንም ክፉ ነገሮችን በማድረግ ነው። እነዚህ ሰዎች የሚጠፉትም ለመዳን የሚያበቃቸውን እውነት ወደው ስላልተቀበሉ ነው።