ምሳሌ 11:27 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መልካምን ነገር ተግቶ የሚሻ መልካም ነገርን ያገኛል፤ ክፉ ነገርን የሚሠራ ግን ክፉ ነገር ይደርስበታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጎ ነገርን ተግቶ የሚሻ በጎ ነገር ይጠብቀዋል፤ ክፉ ነገር የሚፈልገውን ግን ክፉ ያገኘዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መልካምን ተግቶ የሚሻ ደስታን ይፈልጋል፥ ክፉን በሚፈልግ ግን ክፉ ይመጣበታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መልካምን የሚያስብ መልካም ክብርን ይወድዳል። ክፋትን የሚፈልግን ግን ክፋት ታገኘዋለች። |
ጠላቶቼ እኔን ለመያዝ ወጥመድ ዘርግተውብኛል፤ ሁለንተናዬን የሚያጐብጥ ተስፋ መቊረጥ ደረሰብኝ፤ በመንገዴ ጒድጓድ ቈፈሩ፤ ነገር ግን እነርሱ ራሳቸው ወደቁበት።