ምሳሌ 11:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በንቀት ተናግሮ ሰውን የሚያዋርድ፥ ማስተዋል የጐደለው ነው፤ አስተዋይ ሰው ግን ዝም ይላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልበ ቢስ ባልንጀራውን ያንኳስሳል፤ አስተዋይ ግን አንደበቱን ይገዛል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወዳጁን የሚንቅ ልበ ጐደሎ ነው፥ አስተዋይ ሰው ግን ዝም ይላል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጥበብ የጐደለው የሀገሩን ሰው ይንቃል። ብልህ ሰው ግን ጸጥታን ያመጣል። |
ከዚህ በኋላ ዘቡል እንዲህ አለው፤ “ያ ሁሉ ፉከራህ አሁን የት ደረሰ? ‘አቤሜሌክ የተባለውን ሰው የምናገለግለው ለምንድን ነው?’ ብለህ የጠየቅህ አንተ አልነበርክምን? በማፌዝ ስታላግጥባቸው የነበርከው ሰዎች እነሆ፥ እነዚህ ናቸው፤ በል ወጥተህ ጦርነት ግጠማቸው፤”
ነገር ግን አንዳንድ ሥርዓተ አልባዎች “አሁን ይህ ሰው እኛን ለማዳን ይችላል?” ተባባሉ፤ እርሱንም በመናቅ ምንም ዐይነት ገጸ በረከት ሳያመጡለት ቀሩ። ሳኦል ግን ዝም አለ።