ምሳሌ 10:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስንፍና ያደኸያል፤ ተግቶ መሥራት ግን ያበለጽጋል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰነፍ እጆች ሰውን ያደኸያሉ፤ ትጉህ እጆች ግን ብልጽግናን ያመጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የታካች እጅ ችግረኛ ታደርጋለች፥ የትጉ እጅ ግን ሀብታም ታደርጋለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሐኬተኛ እጅ ችግረኛ ያደርጋል፤ የትጉህ እጅ ግን ባለጠጋ ያደርጋል። |
አንዳንድ ሰዎች በለጋሥነት ገንዘባቸውን ይበትናሉ፤ ነገር ግን ሀብታቸው እየበዛ ይሄዳል፤ ሌሎች ደግሞ ያለ ልክ ለገንዘባቸው ይሳሳሉ፤ ነገር ግን ድኽነታቸው እየበዛ ይሄዳል።
ለሚጠፋ ምግብ አትሥሩ፤ ይልቅስ እግዚአብሔር አብ የማረጋገጫ ማኅተም ስለ አተመው የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ፥ የዘለዓለም ሕይወት ለሚሆነው ምግብ ሥሩ።”
ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ፤ ለጌታ ሥራ የምትደክሙት በከንቱ አለመሆኑን ዐውቃችሁ፥ ሳታቋርጡ ዘወትር የጌታን ሥራ ለመሥራት ትጉ።