ምሳሌ 10:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የደግ ሰው ንግግር እንደ ነጠረ ብር ነው፤ የክፉ ሰው አሳብ ግን ዋጋቢስ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጻድቅ አንደበት የነጠረ ብር ነው፤ የክፉ ሰው ልብ ግን ርባና የለውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጻድቅ ምላስ የተፈተነ ብር ነው፥ የክፉ ልብ ግን ዋጋ ቢስ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጻድቅ ምላስ የተፈተነ ብር ነው፤ የኃጥኣን ልብ ግን ይጐድላል። |
የመሥዋዕቱም መዓዛ እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው፤ በሐሳቡም እንዲህ አለ፥ ገና ከሕፃንነቱ ጊዜ ጀምሮ የሰው ሐሳብ ክፉ መሆኑን ስለማውቅ፤ “ሰው በሚፈጽመው በደል ሁሉ ከእንግዲህ ወዲህ ምድርን አልረግምም፤ በአሁኑ ጊዜ እንዳደረግሁት ሕይወት ያለውን ፍጥረት ሁሉ ከእንግዲህ ወዲህ ከቶ አላጠፋም።