የደግ ሰው ንግግር የሕይወት ምንጭ ነው፤ የክፉ ሰው ንግግር ግን የዐመፅ መሸፈኛ ነው።
የጻድቅ አንደበት የሕይወት ምንጭ ናት፤ መዓት ግን የክፉዎችን አፍ ይዘጋል።
የጻድቅ አፍ የሕይወት ምንጭ ማፍለቂያ ናት፥ የክፉዎች አፍ ግን ዐመፅን ይሸፍናል።
የሕይወት ምንጭ በጻድቃን አፍ ነው፥ የኃጥኣንን አፍ ግን ጥፋት ይከድነዋል።
ቅኖች ይህን በማየት ደስ ይላቸዋል፤ ክፉዎች ግን ዐፍረው ዝም ይላሉ።
የደጋግ ሰዎች ንግግር ተስማሚ ነው፤ የክፉዎች ንግግር ግን ጠማማ ነው።
ደግ ሰው በረከትን ያገኛል፤ ክፉ ሰው ግን ዐመፀኛነቱን በመልካም አነጋገር ይሸፍናል።
የጠቢባን ትምህርት የሕይወት ምንጭ ነው፤ ሕይወትህ በአደጋ ላይ ቢወድቅ እንኳ እንድታመልጥ ይረዳሃል።
ለስላሳ አነጋገር ሕይወትን ይሰጣል። ተንኰል የተሞላበት አነጋገር ግን መንፈስን ይሰብራል።
ዕውቀት የሚስፋፋው በብልኆች እንጂ በሞኞች አይደለም።
ከሰው አንደበት የሚወጣው የጥበብ ንግግር እንደ ጥልቅ ውሃ ነው፤ እንደ ምንጭ ውሃም ጣፋጭ ነው።
ዕውቀት የተሞላበት ንግግር፥ ከወርቅና ከከበረ ዕንቊ ይበልጥ የተወደደ ነው።
ከቶ ከአፋችሁ ክፉ ቃል አይውጣ፤ ነገር ግን ለሚሰሙት ደስ የሚያሰኝና ለማነጽ የሚጠቅም ለሰዎችም አስፈላጊ የሆነውን ቃል ተናገሩ።