ምሳሌ 1:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም መከራ በእናንተ ላይ በሚደርስባችሁ ጊዜ እስቅባችኋለሁ፤ ችግር በሚደርስባችሁም ጊዜ አፌዝባችኋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ ደግሞ በመከራችሁ እሥቅባችኋለሁ፤ መዓት በሚወርድባችሁም ጊዜ አፌዝባችኋለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔም በእናንተ መጥፋት እስቃለሁ፥ ሽብር በመጣባችሁ ጊዜ አላግጥባችኋለሁ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ እኔ በጥፋታችሁ እሥቃለሁ፤ ጥፋትም በመጣባችሁ ጊዜ ደስ ይለኛል። |
እግዚአብሔር እናንተን ለማበልጸግና ቊጥራችሁንም ለማብዛት እንደ ወደደው ሁሉ እንደገናም እናንተን በማጥፋትና በመደምሰስ ደስ ይለዋል። ከዚህች ከምትወርሱአት ምድር ተነቃቅላችሁ ትጠፋላችሁ።