ምሳሌ 1:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልጄ ሆይ! እነዚህን ከመሰሉ ሰዎች ጋር አብረህ አትሂድ፤ ከእነርሱም ራቅ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጄ ሆይ፤ ዐብረሃቸው አትሂድ፤ በሚሄዱበትም መንገድ እግርህን አታንሣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልጄ ሆይ፥ ከእነርሱ ጋር በመንገድ አትሂድ፥ ከጎዳናቸውም እግርህን አርቅ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልጄ ሆይ፥ ከእነርሱ ጋር በመንገድ አትሂድ፥ ከጎዳናቸውም እግርህን ፈቀቅ አድርግ፤ |
በእውነትና በትክክል የሚናገሩ፥ በግፍ የሚገኝን ትርፍ የሚጸየፉ፥ ጉቦን ከመቀበል ይልቅ የሚያስወግዱ፥ ስለ ነፍስ ግድያ መስማት የማይፈልጉና፥ ክፉ ነገርን ከማየት ዐይኖቻቸውን የሚጨፍኑ፥
እግዚአብሔር ስለ እነዚህ ሕዝብ እንዲህ ይላል፦ “ከእኔ ርቀው መሄድ ይወዳሉ፤ ራሳቸውንም አይቈጣጠሩም፤ ስለዚህ እኔ በእነርሱ ደስ አልሰኝም፤ የፈጸሙትን በደል ሁሉ በማስታወስ ስለ ኃጢአታቸው እቀጣቸዋለሁ።”