ምሳሌ 1:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምናልባትም እንዲህ ይሉህ ይሆናል፦ “ከበደል ንጹሕ የሆነውን ሰው መንገድ ላይ አድብተን እንድንገድለው ከእኛ ጋር ና! አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ከእኛ ጋራ ናና፣ ደም ለማፍሰስ እናድባ፤ በደል በሌለበት ሰው ላይ እንሸምቅ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደምን ለማፍሰስ “ና እናድባ፥ ለንጹሕም ያለ ምክንያት ወጥመድን እንሸምቅበት” ቢሉ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ና ከእኛ ጋር ደምን በማፍሰስ አንድ ሁን፥ ጻድቅ ሰውንም በምድር እንቅበር፥ ብለው ቢማልዱህ፥ |
ወደ ዕርድ እንደሚሄድ የበግ ጠቦት ሆኜ ነበር፤ እነርሱ “ስሙ ዳግመኛ እንዳይታወስ ዛፉን ከነፍሬው እናጥፋ፤ ከሕያዋያን ዓለም እናስወግደው” ብለው በእኔ ላይ ማደማቸውን አላወቅሁም ነበር።
“በሕዝቤ መካከል የሚኖሩ ክፉ ሰዎች አሉ፤ እነርሱም ወፎችን በወጥመድ እንደሚይዝ ሰው ናቸው፤ ስለዚህ ሰዎችን ለማጥመድ መረባቸውን ዘርግተው ያደባሉ።
ከምድሪቱ ላይ ታማኝ ሰው ጠፍቶአል፤ አንድም ትክክለኛ ሰው የለም፤ ሁላቸውም ሰውን ለመግደል ያደባሉ፤ እርስ በርሳቸውም አንዱ ሌላውን ተከታትሎ ያጠምዳል።
ስለዚህ እናንተ ከሸንጎው ጋር ተስማምታችሁ በጥብቅ የምትመረምሩት ነገር እንዳለ በማስመሰል ጳውሎስን እንዲያመጡላችሁ አዛዡን ጠይቁት፤ እኛም እዚህ ከመድረሱ በፊት ልንገድለው ተዘጋጅተናል።”