ጳውሎስ ወደ ደርቤና ወደ ልስጥራ ሄደ፤ በልስጥራ ጢሞቴዎስ የሚባል አማኝ ይኖር ነበር፤ እናቱ አይሁዳዊት ክርስቲያን ነበረች፤ አባቱ ግን አረማዊ ነበር።
ፊልሞና 1:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ እስረኛ ከሆንኩ ከእኔ ከጳውሎስና ከወንድማችን ከጢሞቴዎስ፥ ለተወደደው ወንድማችንና የሥራ ጓደኛችን ለሆነው ለፊልሞና፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የክርስቶስ ኢየሱስ እስረኛ ከሆነው ከጳውሎስና ከወንድማችን ከጢሞቴዎስ፤ ለተወደደው እና ዐብሮን ለሚሠራው ለፊልሞና፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ እስረኛ ከሆነው ጳውሎስና ከወንድሙ ጢሞቴዎስ፥ ለተወደደውና አብሮን ለሚሠራ ለፊልሞና፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የክርስቶስ ኢየሱስ እስረኛ ጳውሎስ ወንድሙም ጢሞቴዎስ፥ ለተወደደውና አብሮን ለሚሠራ ለፊልሞና፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የክርስቶስ ኢየሱስ እስር ጳውሎስ ወንድሙም ጢሞቴዎስ፥ ለተወደደውና አብሮን ለሚሠራ ለፊልሞና፥ |
ጳውሎስ ወደ ደርቤና ወደ ልስጥራ ሄደ፤ በልስጥራ ጢሞቴዎስ የሚባል አማኝ ይኖር ነበር፤ እናቱ አይሁዳዊት ክርስቲያን ነበረች፤ አባቱ ግን አረማዊ ነበር።
በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስና ከወንድማችን ከጢሞቴዎስ፥ በቆሮንቶስ ለምትገኘው የእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንና እንዲሁም በመላው አካይያ ለሚገኙ ሕዝበ ክርስቲያን ሁሉ፥
የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋዮች ከሆኑት ከጳውሎስና ከጢሞቴዎስ፥ በፊልጵስዩስ ከተማ ለሚኖሩ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱሳን ለሆኑ ሁሉ፥ እንዲሁም ለኤጲስ ቆጶሳትና ዲያቆናት፦
እንዲሁም እኔን በሚያስፈልገኝ ሁሉ እንዲረዳኝ ልካችሁት የነበረውን ወንድሜን ኤጳፍሮዲቱስን ወደ እናንተ መላክ አስፈላጊ ሆኖ አግኝቼዋለሁ፤ እርሱ ከእኔ ጋር የተሰለፈ ወታደርና የሥራ ጓደኛዬ ሆኖ ሲሠራ የቈየ ነው።
አንተም እዚያ ያለኸው ታማኝ የሥራ ጓደኛዬ እነዚህን ሴቶች እንድትረዳቸው እለምንሃለሁ፤ እነዚህ ሴቶች ከእኔ ጋር ከቀሌምንጦስና ስሞቻቸው በሕይወት መጽሐፍ ከተጻፉት ከሌሎችም የሥራ ጓደኞቼ ጋር በመሆን ወንጌልን በማዳረስ ረገድ ተጋድለዋል።
ኢዮስጦስ ተብሎም የሚጠራው ኢያሱ ሰላምታ ያቀርብላችኋል። ስለ እግዚአብሔር መንግሥት ከእኔ ጋር አብረው ከሚሠሩት ሰዎች መካከል የአይሁድ ወገኖች የሆኑት እነዚህ ብቻ ናቸው፤ እኔንም አጽናንተውኛል።
ወንድማችንንና የእግዚአብሔር አገልጋይ የሆነውን፥ የክርስቶስን መልካም ዜና በማብሠር የሥራ ጓደኛችንን ጢሞቴዎስን ልከንላችኋል፤ የላክንላችሁም እንዲያጸናችሁና በእምነት እንድትበረቱ እንዲመክራችሁ ነው፤
የእግዚአብሔር የአባታችንና የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ለሆነችው ለተሰሎንቄ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ከጳውሎስ፥ ከሲላስና ከጢሞቴዎስ የተላከ፦
እንግዲህ ስለ ጌታችን ለመመስከር አትፈር፤ ስለ እርሱ በታሰርኩት በእኔም አትፈር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር በሚሰጥህ ኀይል ስለ ወንጌል ከእኔ ጋር መከራን ተቀበል።