የሁለተኛው ወር በገባ በዐሥራ አራተኛው ቀን የበግ ጠቦቶችን ለፋሲካ በዓል መሥዋዕት አድርገው ዐረዱ፤ በዚህ ጊዜ ራሳቸውን ያላነጹ ካህናትና ሌዋውያን በጣም አፈሩ፤ ከዚህም የተነሣ ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ለዩ፤ ከዚያም በኋላ በቤተ መቅደሱ ውስጥ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ማቅረብ ቻሉ።
ዘኍል 9:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን ምሽት በሕጉና በሥርዓቱ መሠረት ሥርዓቱን ይፈጽሙ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዓሉንም በዚህ ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን ፀሓይ በምትጠልቅበት ጊዜ በተወሰነው ሕግና ሥርዐት መሠረት ሁሉ አክብሩ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ ወር በዓሥራ አራተኛው ቀን ምሽት ላይ፥ በተወሰነለት ጊዜ ታደርጉታላችሁ፤ እንደ ሥርዓቱ ሁሉ እንደ ደንቡም ሁሉ ታደርጉታላችሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመጀመሪያው ወር በዐሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ በጊዜው አድርጉት፤ እንደ ሥርዐቱ ሁሉ እንደ ፍርዱም ሁሉ አድርጉት።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚህ ወር በአሥራ አራተኛው ቀን በመሸ ጊዜ በጊዜው አድርጉት፤ እንደ ሥርዓቱ ሁሉ እንደ ፍርዱም ሁሉ አድርጉት። |
የሁለተኛው ወር በገባ በዐሥራ አራተኛው ቀን የበግ ጠቦቶችን ለፋሲካ በዓል መሥዋዕት አድርገው ዐረዱ፤ በዚህ ጊዜ ራሳቸውን ያላነጹ ካህናትና ሌዋውያን በጣም አፈሩ፤ ከዚህም የተነሣ ራሳቸውን ለእግዚአብሔር ለዩ፤ ከዚያም በኋላ በቤተ መቅደሱ ውስጥ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ማቅረብ ቻሉ።
ንጉሥ ኢዮስያስ በኢየሩሳሌም ለእግዚአብሔር ክብር የፋሲካን በዓል አከበረ፤ የመጀመሪያው ወር በገባ በዐሥራ አራተኛው ቀን ሕዝቡ የፋሲካን በግ ዐረደ፤
እንዲህማ ቢሆን ኖሮ ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ብዙ ጊዜ መከራ መቀበል ባስፈለገው ነበር፤ አሁን ግን በዘመናት መጨረሻ ኃጢአትን ለማስወገድ ራሱን መሥዋዕት በማድረግ አንዴ በማያዳግም ሁኔታ ተገልጦአል።