ዘኍል 9:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ድንኳናቸውን የሚተክሉትም ሆነ ሰፈር ለቀው ወደ ፊት የሚጓዙት እግዚአብሔር ለሙሴ በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእግዚአብሔር ትእዛዝ ይሰፍራሉ፤ በእግዚአብሔርም ትእዛዝ ይጓዛሉ፤ እነርሱም በሙሴ አማካይነት የተሰጠውን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ይጠብቁ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጌታ ትእዛዝ ይሰፍሩ ነበር፥ በጌታም ትእዛዝ ይጓዙ ነበር፥ ጌታ በሙሴ አንደበት እንዳዘዘ የጌታን ትእዛዝ ይጠብቁ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእግዚአብሔር ትእዛዝ ይሰፍሩ ነበር፤ በእግዚአብሔርም ትእዛዝ ይጓዙ ነበር፤ እግዚአብሔር በሙሴ ቃል እንደ አዘዘ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ይጠብቁ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእግዚአብሔር ትእዛዝ ይሰፍሩ ነበር፥ በእግዚአብሔርም ትእዛዝ ይጓዙ ነበር፥ እግዚአብሔር በሙሴ እጅ እንዳዘዘ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ይጠብቁ ነበር። |
መላው የእስራኤል ሕዝብ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ከቦታ ወደ ቦታ በመዘዋወር “ሲን” ተብሎ የሚጠራውን ምድረ በዳ ትተው በረፊዲም ሰፈሩ፤ ነገር ግን በዚያ የሚጠጣ ውሃ አልነበረም።
እንዲሁም በሸለቆው ውስጥ እንደሚሄድ የከብት መንጋ የእግዚአብሔር መንፈስ ዕረፍትን ሰጣቸው። ስምህ ይከብር ዘንድ ሕዝብህን በዚህ ዐይነት መራሃቸው።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል አለው፦ “አካሄድህ እንደኔ ፈቃድ ቢሆን፥ ያዘዝኩህንም ሁሉ ብታደርግ፥ በቤተ መቅደሴ የአስተዳዳሪነትን፥ በአደባባዮቼም የበላይነትን ሥልጣን እሰጥሃለሁ፤ እዚህ ከቆሙት መላእክት ጋር በእኔ ፊት መግባትና መውጣት እንድትችል ባለሟልነትን እሰጥሃለሁ።