እንዲሁም እግዚአብሔር የሚመለክበትን ድንኳንና ቤተ መቅደሱን የመንከባከብ ኀላፊነት የእነርሱ ነበር፤ በተጨማሪም በቤተ መቅደሱ ውስጥ በሚፈጸመው የአምልኮ ሥነ ሥርዓት ዘመዶቻቸውን የአሮን ዘሮች የሆኑ ካህናትን ይረዱ ነበር።
ዘኍል 8:26 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያ በኋላ ወንድሞቻቸው ሌዋውያን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለሚፈጽሙት አገልግሎት እንደ ረዳት ሆነው ይሠራሉ፤ እነርሱ ራሳቸው ብቻቸውን ግን ምንም ዐይነት ሥራ አይሥሩ፤ እንግዲህ የሌዋውያንን አገልግሎት ሥርዓት የምታስይዘው በዚህ ዐይነት ነው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያ በኋላ ወንድሞቻቸው በመገናኛው ድንኳን ሥራቸውን በሚያከናውኑበት ጊዜ ያግዟቸዋል እንጂ ራሳቸው መሥራት የለባቸውም። ኀላፊነታቸውን እንዲወጡ የምታሰማራቸው በዚህ መልኩ ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድሞቻቸው የተሰጣቸውን ግዴታ እንዲወጡ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ይርዱአቸው እንጂ የድንኳኑን አገልግሎት አይሠሩ። በየአገልግሎታቸው በመደልደል በሌዋውያን ላይ እንዲሁ ታደርጋለህ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድሙንም በምስክሩ ድንኳን ውስጥ ያገልግል፤ ሰሞናቸውንም ይጠብቅ። ነገር ግን አገልግሎቱን ይተው። እንዲሁ በየሰሞናቸው ለሌዋውያን ታደርጋለህ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተሰጣቸውን ይጠብቁ ዘንድ ወንድሞቻቸውን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ያገለግላሉ፤ የድንኳኑን አገልግሎት አይሠሩም። እንዲሁ ስለ ሥራቸው በሌዋውያን ላይ ታደርጋለህ። |
እንዲሁም እግዚአብሔር የሚመለክበትን ድንኳንና ቤተ መቅደሱን የመንከባከብ ኀላፊነት የእነርሱ ነበር፤ በተጨማሪም በቤተ መቅደሱ ውስጥ በሚፈጸመው የአምልኮ ሥነ ሥርዓት ዘመዶቻቸውን የአሮን ዘሮች የሆኑ ካህናትን ይረዱ ነበር።
እነርሱ በቤተ መቅደሱ በር ጠባቂነት፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ሰዎች የሚያቀርቡአቸውን መሥዋዕቶች በማረድ፥ እንዲሁም ሰዎችን በማገልገል እንዲሠሩ ይፈቅድላቸዋል።
ነገር ግን ማንም ሰው ወደ ድንኳኑ በመቅረብ ቊጣዬን አነሣሥቶ የእስራኤልን ማኅበር እንዳያስፈጅ ሌዋውያን በድንኳኑ ዙሪያ ሰፍረው ይጠብቁት።”
እነርሱ ዘወትር ከእናንተ ጋር መሥራትና በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ስለ ተሰጣቸው አገልግሎት ሁሉ ኀላፊነታቸውን መፈጸም አለባቸው፤ ነገር ግን ሌዋዊ ያልሆነ ማንኛውም ሰው ለመሥራት ወደ እናንተ መቅረብ የለበትም።
ለቀሩት የማኅበሩ አባላት ከተሰጠውም ክፍል ከኀምሳ እስረኞች አንዱን፥ በዚሁ መጠን ከከብቱ፥ ከአህዮቹ፥ ከበጎቹና ከፍየሎቹ ለይታችሁ ለተቀደሰው ድንኳን ኀላፊዎች ለሆኑት ሌዋውያን ስጡ።”