ለአገልግሎት ወደ ውስጠኛው አደባባይ፥ ወደ መቅደሱ በሚገባበት ቀን ለኃጢአቱ መሥዋዕት ያቅርብ፤ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።
ዘኍል 6:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በድንገት አንድ ሰው በአጠገቡ ቢሞት፥ የተቀደሰውን ራሱንም ቢያረክስ፥ በሰባተኛው ቀን ራሱን ይላጭ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘ድንገት ሰው አጠገቡ ሞቶ ለእግዚአብሔር የተለየበትን ጠጕሩን ቢያረክስበት፣ በሚነጻበት ዕለት ማለት በሰባተኛው ቀን ጠጕሩን ይላጭ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ሰውም በአጠገቡ ድንገት ቢሞት እርሱም የተቀደሰውን ራሱን ቢያረክስ፥ እርሱ በሚነጻበት ቀን ራሱን ይላጫል፤ በሰባተኛው ቀን ይላጨዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ሰውም በአጠገቡ ድንገት ቢሞት የራሱ ብፅዐት ይረክሳል፤ እርሱ በሚነጻበት ቀን ራሱን ይላጭ፤ በሰባተኛው ቀን ይላጨው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰውም በአጠገቡ ድንገት ቢሞት የተለየውንም ራሱን ቢያረክስ፥ እርሱ በሚነጻበት ቀን ራሱን ይላጭ፤ በሰባተኛው ቀን ይላጨው። |
ለአገልግሎት ወደ ውስጠኛው አደባባይ፥ ወደ መቅደሱ በሚገባበት ቀን ለኃጢአቱ መሥዋዕት ያቅርብ፤ እኔ ልዑል እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።
ከበሽታው የነጻው ሰው ልብሱን ያጥባል፤ ጠጒሩን ሁሉ ይላጫል፤ ሰውነቱንም ይታጠባል፤ ከዚያም በኋላ የነጻ ሆኖ ወደ ሰፈር ይገባል፤ ነገር ግን እስከ ሰባት ቀን ከራሱ ድንኳን ውጪ መቈየት አለበት።
በሰባተኛውም ቀን እንደገና ራሱን፥ ጢሙን፥ ቅንድቡንና በሌላውም ሰውነት ላይ ያለውን ጠጒር ሁሉ ተላጭቶ ልብሱን በውሃ ይጠብ፤ ሰውነቱንም ይታጠብ፤ ከዚያም በኋላ የነጻ ይሆናል።
ጳውሎስ ከወንድሞች ጋር ብዙ ቀኖች በቆሮንቶስ ከቈየ በኋላ ተሰናብቶአቸው ወደ ሶርያ ሄደ፤ ጵርስቅላና አቂላም ከእርሱ ጋር ነበሩ፤ ነገር ግን ስለት ስለ ነበረበት ከመሄዱ በፊት ክንክሪያ በሚባል ቦታ ራሱን ተላጨ።