ንጉሥ ዖዝያ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ የቆዳው በሽታ አለቀቀውም፤ ይህም በመሆኑ በተለየ ቤት ኖረ፤ ከእግዚአብሔርም ቤት እንዲገለል ተደረገ፤ ልጁ ኢዮአታም የቤተ መንግሥቱ ኀላፊ በመሆን የአገሪቱን ሕዝብ ያስተዳድር ነበር።
ዘኍል 5:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው እስራኤላውያን ከሰፈሩ አስወጡአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስራኤላውያን ይህንኑ አደረጉ፤ ሰዎቹንም ከሰፈር አስወጧቸው፤ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘውም መሠረት ፈጸሙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልም ልጆች እንዲሁ አደረጉ፥ እነርሱንም ከሰፈሩ አወጡአቸው፤ ጌታ ሙሴን እንደ ተናገረው፥ የእስራኤል ልጆች እንዲሁ አደረጉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ልጆች እንዲሁ አደረጉ፤ ከሰፈሩ አወጡአቸው፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንደ ተናገረው፥ የእስራኤል ልጆች እንዲሁ አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ልጆች እንዲሁ አደረጉ፥ ከሰፈሩ አወጡአቸው፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንደ ተናገረው፥ የእስራኤል ልጆች እንዲሁ አደረጉ። |
ንጉሥ ዖዝያ እስከ ዕለተ ሞቱ ድረስ የቆዳው በሽታ አለቀቀውም፤ ይህም በመሆኑ በተለየ ቤት ኖረ፤ ከእግዚአብሔርም ቤት እንዲገለል ተደረገ፤ ልጁ ኢዮአታም የቤተ መንግሥቱ ኀላፊ በመሆን የአገሪቱን ሕዝብ ያስተዳድር ነበር።
በመካከላቸው እኔ የምኖርበትን ሰፈራቸውን እንዳያረክሱ፥ እነዚህን ያልነጹ ሰዎች ሁሉ ወንዶችም ሆኑ ሴቶች ከመካከላችሁ ወጥተው እንዲባረሩ አድርጉ።”