La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 4:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በመገናኛው ድንኳን ለማገልገል ብቃት ያላቸውን፥ ዕድሜአቸው ከሠላሳ እስከ ኀምሳ ዓመት የሆናቸውን ወንዶች ሁሉ ቊጠር፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከሠላሳ እስከ ዐምሳ ዓመት የሆናቸውን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ይሠሩ ዘንድ ለማገልገል የሚመጡትን ወንዶች ሁሉ ቍጠር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሥራን ለመሥራት ወደ አገልግሎት የሚገቡትን ሁሉ ዕድሜአቸው ከሠላሳ ዓመት ጀምሮ እስከ ኀምሳ ዓመት ድረስ ያሉትን ቁጠራቸው።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የም​ስ​ክ​ሩን ድን​ኳን ሥራ ይሠሩ ዘንድ ለአ​ገ​ል​ግ​ሎት የሚ​ገ​ቡ​ትን ሁሉ ከሃያ አም​ስት ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ቍጠ​ራ​ቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የመገናኛውን ድንኳን ሥራ ይሠሩ ዘንድ ለአገልግሎት የሚገቡትን ሁሉ ከሠላሳ ዓመት ጀምሮ እስከ አምሳ ዓመት ድረስ ቍጠራቸው።

Ver Capítulo



ዘኍል 4:23
18 Referencias Cruzadas  

እንግዲህ እነዚህ ሁሉ በየጐሣቸውና በየቤተሰባቸው የተዘረዘሩት የሌዊ ዘሮች ሲሆኑ፥ እያንዳንዳቸው በየስማቸው ተጠቅሰዋል። ኻያ ዓመት የሞላው ወይም ከዚያ በላይ የሆነው እያንዳንዱ የሌዊ ዘር በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ባለው ሥራ ድርሻ ነበረው።


ዳዊት ለመጨረሻ ጊዜ በሰጠው መመሪያ መሠረት ሌዋውያን ሁሉ ኻያ ዓመት የሞላቸውና ከዚያ በላይ የሆኑ ተመዘገቡ፤


ዕድሜአቸው ሠላሳና ከዚያም በላይ የሆኑትን ሌዋውያን ወንዶችን ቈጠረ፤ ጠቅላላ ድምራቸውም ሠላሳ ስምንት ሺህ ሆነ፤


“የጌርሾን ጐሣዎች የሆኑትን ሌዋውያን በየትውልዳቸውና በየቤተሰባቸው ቊጠራቸው፤


እነርሱ ልዩ ልዩ ዕቃዎችን የመሸከም ኀላፊነት ይኖራቸዋል።


በመገናኛው ድንኳን ለማገልገል ብቃት ያላቸውን፥ ዕድሜአቸው ከሠላሳ እስከ ኀምሳ የሚደርሰውን ወንዶች ሁሉ መዝግብ።


ኀምሳ ዓመት ሲሞላላቸው የአገልግሎት ሥራቸውን ይተዋሉ፤ ከዚያም በኋላ አይሠሩም።


ያለ ደመወዝ በራሱ ገንዘብ በወታደርነት የሚያገለግል ማነው? ወይን ተክሎ ፍሬውን የማይበላስ ማነው? መንጋ እየጠበቀ የመንጋውን ወተት የማይጠጣ ማን ነው?


በእውነት ቃልና በእግዚአብሔር ኀይል ነው። የማጥቂያም ሆነ የመከላከያ መሣሪያችን ጽድቅ ነው፤


የሥጋ ምኞት ከመንፈስ ምኞት ጋር ይቃረናል፤ መንፈስና ሥጋ እርስ በእርሳቸው ይቃረናሉ፤ ስለዚህ እናንተ የምትፈልጉትን ማድረግ አትችሉም፤


የኢየሱስ ክርስቶስ የሆኑት ሰዎች ሥጋን ከፍትወቱና ከምኞቱ ጋር ሰቅለውታል።


ልጄ ጢሞቴዎስ ሆይ! ከዚህ ቀደም ስለ አንተ በትንቢት በተነገረው መሠረት የሚከተለውን ትእዛዝ በዐደራ እሰጥሃለሁ፤ ትንቢቱን በመከተል መልካም ጦርነትን ተዋጋ፤


ጦርነትን በመልካም ተዋግቻለሁ፤ የእሽቅድድም ሩጫዬን እስከ መጨረሻው ሮጫለሁ፤ እምነትን ጠብቄአለሁ።