ናኮን ተብሎ ወደሚጠራውም አውድማ በደረሱ ጊዜ ሠረገላውን የሚስቡት በሬዎች ስለ ነቀነቁት ዑዛ እጁን ዘርግቶ የቃል ኪዳኑ ታቦት እንዳይወድቅ ደገፈ፤
ዘኍል 4:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ተቀደሰው ስፍራ ተጠግተው እንዳይሞቱ እንዲህ አድርግላቸው፦ አሮንና ልጆቹ ወደ መቅደሱ ገብተው የያንዳንዱን ሰው ሥራና ሸክሙን ይመድቡለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ንዋየ ቅድሳቱ በሚቀርቡበትም ጊዜ በሕይወት እንዲኖሩ እንጂ እንዳይሞቱ አንተ ይህን አድርግላቸው፤ አሮንና ልጆቹ ወደ መቅደሱ ይግቡ፤ እያንዳንዱንም ሰው በየሥራው ላይ ይደልድሉት፤ ምን መሸከም እንዳለበትም ያስታውቁት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን እጅግ ቅዱስ ወደ ሆኑት ነገሮች በቀረቡ ጊዜ በሕይወት እንዲኖሩ እንጂ እንዳይሞቱ እንዲህ አድርጉላቸው፦ አሮንና ልጆቹ ይግቡ፥ እያንዳንዱንም ሰው በየተግባሩና በየሥራው ጫና ይመድቡት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ በቀረቡ ጊዜ በሕይወት ይኖሩ ዘንድ እንጂ እንዳይሞቱ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ አሮንና ልጆቹ ይግቡ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ወደ ቅድስተ ቅዱሳን በቀረቡ ጊዜ በሕይወት ይኖሩ ዘንድ እንጂ እንዳይሞቱ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ አሮንና ልጆቹ ይግቡ፥ ለሰውም ሁሉ ሥራውንና ሸክሙን ይዘዙ፤ |
ናኮን ተብሎ ወደሚጠራውም አውድማ በደረሱ ጊዜ ሠረገላውን የሚስቡት በሬዎች ስለ ነቀነቁት ዑዛ እጁን ዘርግቶ የቃል ኪዳኑ ታቦት እንዳይወድቅ ደገፈ፤
እግዚአብሔርም እንዲህ አለው፤ “እኔን እግዚአብሔርን ለማየት የተወሰነውን ክልል አልፈው እንዳይመጡ ወርደህ ለሕዝቡ ንገር፤ ይህን ቢያደርጉ ግን ከእነርሱ ብዙዎቹ ይሞታሉ፤
ሰፈራችሁን ለቃችሁ በምትሄዱበት ጊዜ ሌዋውያን ብቻ ድንኳኑን ነቅለው በሚሰፍሩበት አዲስ ቦታ ይተክሉታል፤ ከእነርሱ በቀር ወደ ድንኳኑ የሚቀርብ ማንኛውም ሰው በሞት ይቀጣል።
እነርሱም እናንተን የመርዳት ተግባራቸውን እያከናወኑ ድንኳኑንም የመንከባከብ ኀላፊነት ይወስዳሉ፤ ይሁን እንጂ በተቀደሰው ስፍራና በመሠዊያው ላይ ያሉትን ንዋያተ ቅድሳት መንካት አይኖርባቸውም፤ ነክተው ቢገኙ ግን እነርሱም እናንተም በአንድነት ትሞታላችሁ።
ከሰፈር በሚነሡበትም ጊዜ አሮንና ልጆቹ ንዋያተ ቅድሳቱንና የእነርሱንም መገልገያ ዕቃዎች ሁሉ ከሸፈኑ በኋላ የቀዓት ልጆች መጥተው ይሸከሙአቸው፤ ነገር ግን እንዳይሞቱ ንዋያተ ቅድሳቱን መንካት አይገባቸውም፤ እንግዲህ የመገናኛው ድንኳን በሚነሣበት ጊዜ ሁሉ የቀዓት ልጆች ኀላፊነት ይህ ነው።