Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘኍል 4:19 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ነገር ግን ወደ ቅድስተ ቅዱሳን በቀረቡ ጊዜ በሕይወት ይኖሩ ዘንድ እንጂ እንዳይሞቱ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ አሮንና ልጆቹ ይግቡ፥ ለሰውም ሁሉ ሥራውንና ሸክሙን ይዘዙ፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ወደ ንዋየ ቅድሳቱ በሚቀርቡበትም ጊዜ በሕይወት እንዲኖሩ እንጂ እንዳይሞቱ አንተ ይህን አድርግላቸው፤ አሮንና ልጆቹ ወደ መቅደሱ ይግቡ፤ እያንዳንዱንም ሰው በየሥራው ላይ ይደልድሉት፤ ምን መሸከም እንዳለበትም ያስታውቁት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ነገር ግን እጅግ ቅዱስ ወደ ሆኑት ነገሮች በቀረቡ ጊዜ በሕይወት እንዲኖሩ እንጂ እንዳይሞቱ እንዲህ አድርጉላቸው፦ አሮንና ልጆቹ ይግቡ፥ እያንዳንዱንም ሰው በየተግባሩና በየሥራው ጫና ይመድቡት፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 ወደ ተቀደሰው ስፍራ ተጠግተው እንዳይሞቱ እንዲህ አድርግላቸው፦ አሮንና ልጆቹ ወደ መቅደሱ ገብተው የያንዳንዱን ሰው ሥራና ሸክሙን ይመድቡለት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ነገር ግን ወደ ቅድ​ስተ ቅዱ​ሳኑ በቀ​ረቡ ጊዜ በሕ​ይ​ወት ይኖሩ ዘንድ እንጂ እን​ዳ​ይ​ሞቱ እን​ዲሁ አድ​ር​ጉ​ላ​ቸው፤ አሮ​ንና ልጆቹ ይግቡ፤

Ver Capítulo Copiar




ዘኍል 4:19
6 Referencias Cruzadas  

ወደ ናኮንም አውድማ በደረሱ ጊዜ በሬዎቹ ይፋንኑ ነበርና ዖዛ እጁን ዘርግቶ የእግዚአብሔርን ታቦት ያዘ።


እግዚአብሔርም ሙሴን፦ ውረድ፥ እግዚአብሔርን ለማየት ዳርቻውን እንዳያልፉ ከእነርሱም ብዙ እንዳይጠፉ ለሕዝቡ አስጠንቅቃቸው፤


ማደሪያውም ሲነሣ ሌዋውያን ይንቀሉት፤ ማደሪያውም በሰፈረ ጊዜ ሌዋውያን ይትከሉት፤ ሌላ ሰው ግን ቢቀርብ ይገደል።


እነርሱም ትእዛዝህን የድንኳኑንም ሁሉ አገግሎት ይጠብቁ፤ ነገር ግን እንዳይሞቱ፥ እናንተም ደግሞ ከእነርሱ ጋር እንዳትሞቱ፥ እነርሱ ወደ መቅደሱ ዕቃና ወደ መሠዊያው አይቅረቡ።


ከሰፈሩም ሲነሡ፥ አሮንና ልጆቹ መቅደሱንና የመቅደሱን ዕቃ ሁሉ ከሸፈኑ በኋላ፥ በዚያን ጊዜ የቀዓት ልጆች ሊሸከሙት ይመጣሉ፤ እንዳይሞቱ ግን ንዋየ ቅድሳቱን አይንኩ። በመገናኛው ድንኳን ዘንድ የቀዓት ልጆች ሸክም ይህ ነው።


የቀዓትን ወገኖች ነገድ ከሌዋውያን መካከል አታጥፉአቸው፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos