ዘኍል 36:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህ ዐይነት የማንኛውም እስራኤላዊ ርስት ወደ ሌላ ነገድ አይተላለፍም፤ ከገዛ ነገዱ ጋር የተያያዘ ይሆናል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እያንዳንዱ እስራኤላዊም ከቀደሙት አባቶቹ በወረሰው ርስት ይጽና፤ በእስራኤል ከአንዱ ነገድ ወደ ሌላው ነገድ የሚተላለፍ ርስት አይኖርም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህም የእስራኤል ልጆች ርስት ከአንዱ ነገድ ወደ ሌላው ነገድ አይተላለፍ፤ ከእስራኤልም ልጆች እያንዳንዱ የአባቶቹን ነገድ ርስት ይያዝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደዚህም የእስራኤል ልጆች ርስት ከነገድ ወደ ነገድ ምንም አይተላለፍ፤ ከእስራኤልም ልጆች እያንዳንዱ ወደ አባቶቹ ነገድ ርስት ይጠጋ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንደዚህም የእስራኤል ልጆች ርስት ከነገድ ወደ ነገድ ምንም አይተላለፍ፤ ከእስራኤልም ልጆች እያንዳንዱ ወደ አባቶቹ ነገድ ርስት ይጠጋ። |
በእስራኤላዊ ነገድ መካከል ርስት የተካፈለች ማንኛይቱም ሴት ከዚያው ነገድ የሆነ ወንድ ማግባት ይኖርባታል፤ በዚህ ዐይነት እያንዳንዱ እስራኤላዊ የቀድሞ አባቶቹን ርስት በይዞታው ማቈየት ይችላል።”
ንጉሥ ሆይ! የምልህን አድምጠኝ! አንተን በእኔ ላይ ያነሣሣህ እግዚአብሔር ቢሆን ኖሮ፥ መሥዋዕት በማቅረብ ቊጣውን እንዲመልስ ማድረግ በተቻለ ነበር፤ ነገር ግን ይህን ያደረጉት ሰዎች ከሆኑ ሄደህ ባዕዳን አማልክትን አምልክ ብለው እግዚአብሔር ከሰጠኝ ርስት ድርሻ ስላባረሩኝ በእግዚአብሔር ፊት የተረገሙ ይሁኑ።