የእስራኤል ንጉሥ ኢዮርብዓምና በእርሱ እግር የተተኩት ዘሮቹ ሌዋውያንን የእግዚአብሔር ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉ ስላልፈቀዱላቸው ሌዋውያን ወደ ይሁዳና ወደ ኢየሩሳሌም የመጡት የግጦሽ ቦታዎቻቸውንና የቀረውንም ንብረታቸውን ሁሉ ትተው ነው።
ዘኍል 35:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህም ከተሞች የሌዋውያን ይዞታ ሆነው እነርሱ ይኖሩባቸዋል፤ የግጦሽ መሬቱም ለከብቶቻቸውና ለሌሎች እንስሶቻቸው ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከተሞቹ ለእነርሱ መኖሪያ፣ የግጦሽ መሬቱ ለከብቶቻቸው፣ ለበግና ለፍየል መንጎቻቸውና ለሌሎቹም እንስሶቻቸው ይሆናሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲቀመጡባቸውም ከተሞቹ ለእነርሱ ይሆናሉ፤ መሰማሪያቸውም ለከብቶቻቸው ለእንስሶቻቸውም እነርሱም ላሏቸው ነገሮች ሁሉ ይሁን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከተሞቹም ለእነርሱ መኖሪያ ይሆናሉ፤ መሰማርያቸውም ለከብቶቻቸውና ለእንስሶቻቸው ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም በከተሞቹ ውስጥ ይቀመጣሉ፤ መሰምርያቸውም ለከብቶቻቸው ለእንስሶቻቸውም ለእነርሱም ላለው ሁሉ ይሁን። |
የእስራኤል ንጉሥ ኢዮርብዓምና በእርሱ እግር የተተኩት ዘሮቹ ሌዋውያንን የእግዚአብሔር ካህናት ሆነው እንዲያገለግሉ ስላልፈቀዱላቸው ሌዋውያን ወደ ይሁዳና ወደ ኢየሩሳሌም የመጡት የግጦሽ ቦታዎቻቸውንና የቀረውንም ንብረታቸውን ሁሉ ትተው ነው።
ከዚህም ክልል ውስጥ የእያንዳንዱ ማእዘን ርዝመት አምስት መቶ ክንድ ሆኖ አራት ማእዘን ያለው አንድ ቦታ ለቤተ መቅደሱ ይመደባል፤ በዚህም ክልል ዙሪያ ስፋቱ ኀምሳ ክንድ የሆነ ክፍት ቦታ ይኖራል።
በይሁዳ ተራራማ አገር ያለችውን ቂርይትአርባቅ የምትባለውን ከተማ፥ በዙሪያዋ ካለው የግጦሽ መሬት ጋር ሰጡአቸው፤ እርስዋም ኬብሮን ናት፤ ይህም አርባቅ የዐናቅ አባት ነበር።