ዘኍል 33:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከኤታም ተነሥተው በባዓልጸፎን በስተምሥራቅ ወደ ፒሃሒሮት በመመለስ በሚግዶል ፊት ለፊት ሰፈሩ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከኤታም ተነሥተው ከበኣልዛፎን በስተምሥራቅ ወዳለችው ወደ ፊሀሒሮት በመመለስ በሚግዶል አጠገብ ሰፈሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከኤታምም ተጉዘው በበኣልዛፎን ፊት ወደ ነበረች ወደ ፊሀሒሮት ተመለሱ፤ በሚግዶልም ፊት ለፊት ሰፈሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከኤታምም ተጕዘው በኤልሴፎን ፊት ወደ ነበረች በኤሮት በር፤ በመግደሎ ፊት ለፊት ሰፈሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከኤታምም ተጕዘው በበኣልዛፎን ፊት ወደ ነበረች ወደ ፊሀሒሮት ተመለሱ፤ በሚግዶልም ፊት ለፊት ሰፈሩ። |
የግብጽ ሠራዊት በፈረሶችና በሠረገላዎች ከፈረሰኞች ጋር ሆኖ ተከታተላቸው፤ በቀይ ባሕር ፊት ለፊት ባሉት በፒሃሒሮት በባዓልጸፎን አጠገብ በሰፈሩበት ቦታ ደረሱባቸው።