ዘኍል 31:48 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ የሠራዊቱ አዛዦች የነበሩት የሺህ አለቆችና የመቶ አለቆች ወደ ሙሴ ቀርበው እንዲህ አሉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም በኋላ በሰራዊቱ ክፍሎች ላይ የተሾሙት የሻለቆችና የመቶ አለቆች ወደ ሙሴ ቀርበው፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በብዙ ሺህ በሚቆሩት ሠራዊት ላይ የተሾሙት የጦር አዛዦች፥ ሻለቆችና የመቶ አለቆች፥ ወደ ሙሴ ቀረቡ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሠራዊት አእላፋት ላይ የተሾሙት አለቆች፥ ሻለቆችና የመቶ አለቆች ወደ ሙሴ ቀረቡ፤ ሙሴንም እንዲህ አሉት፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሠራዊት አእላፋት ላይ የተሾሙት አለቆች፥ ሻለቆችና የመቶ አለቆች፥ ወደ ሙሴ ቀረቡ፥ |
ከዚህም ድርሻ ሙሴ ከኀምሳው አንድ እስረኛ፥ ከኀምሳው አንድ እንስሳ ወስዶ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት በእግዚአብሔር ድንኳን ላይ ኀላፊነት ላላቸው ለሌዋውያን ሰጠ።
“ከዚህ በኋላ የጦር መሪዎች ለዘማቾች እንዲህ ይበሉ፤ ‘አዲስ ቤት የሠራና አስመርቆ ያልገባበት ሰው በመካከላችሁ ይገኛልን? ይህ ከሆነ እርሱ ወደ ቤቱ ይመለስ፤ እርሱ በጦርነት ላይ ቢሞት ሌላ ሰው ቤቱን አስመርቆ ይገባበታል።