በሀብትም በኩል ሰባት ሺህ በጎች፥ ሦስት ሺህ ግመሎች፥ አምስት መቶ ጥማድ በሬዎችና አምስት መቶ አህዮች ነበሩት፤ እንዲሁም እጅግ ብዙ አገልጋዮች ነበሩት፤ በምሥራቅ አገር ካሉት ሰዎች ሁሉ እርሱን የሚያኽል ሀብታምና ታላቅ ሰው አልነበረም።
ዘኍል 31:32 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለራሳቸው ካስቀሩት ጭምር ወታደሮቹ የማረኩት ንብረት ዝርዝር የሚከተለው ነው፦ ስድስት መቶ ሰባ አምስት ሺህ በጎች፥ ሰባ ሁለት ሺህ የቀንድ ከብቶች፥ ሥልሳ አንድ ሺህ አህዮችና፥ ሥልሳ ሁለት ሺህ ከወንድ ጋር ግንኙነት ያላደረጉ ሴቶች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወታደሮቹ ማርከው ከወሰዱለት ምርኮ ውስጥ የቀረው ይህ ነበር፤ ስድስት መቶ ሰባ ዐምስት ሺሕ በግ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወታደሮቹም ከወሰዱት ብዝበዛ ያስቀሩት ምርኮ ይህ ነበር፤ ስድስት መቶ ሰባ አምስት ሺህ በጎች፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ሰልፍ የወጡ ሰዎችም ከወሰዱት ብዝበዛ የቀረው ምርኮ እንዲህ ሆነ፤ ስድስት መቶ ሰባ አምስት ሺህ በጎች፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ሰልፍ የወጡ ሰዎችም ከወሰዱት ብዝበዛ ያስቀሩት ምርኮ እንዲህ ሆነ፤ ስድስት መቶ ሰባ አምስት ሺህ በጎች፥ |
በሀብትም በኩል ሰባት ሺህ በጎች፥ ሦስት ሺህ ግመሎች፥ አምስት መቶ ጥማድ በሬዎችና አምስት መቶ አህዮች ነበሩት፤ እንዲሁም እጅግ ብዙ አገልጋዮች ነበሩት፤ በምሥራቅ አገር ካሉት ሰዎች ሁሉ እርሱን የሚያኽል ሀብታምና ታላቅ ሰው አልነበረም።